top of page

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚያስተዳድራቸው መ/ቤቶች የተገኘባቸውን የኦዲት ከፍተቶች በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ የሚያስገድድ መመሪያ ወጣ፡፡

  • Jul 1
  • 2 min read

ሰኔ 24/2018


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚያስተዳድራቸው መስሪያ ቤቶች የተገኘባቸውን የኦዲት ከፍተቶች በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ የሚያስገድድ መመሪያ ወጣ፡፡


የኦዲት መረጃዎችን ማየት የፈለገ ማንኛውም አካል ደግሞ የኦዲት አድራጊ መስሪያ ቤቶችን ኃላፊዎች ፍቃድ ማግኘት ግዴታ አለበት ይላል መመሪያው፡፡


የመንግስት ንብረት ኦዲት መመሪያ ቁጥር190/2018 ኦዲት ተደራጊ መስሪያ ቤት ሥራ አመራርና የህንፃና ንብረት ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣታቸውን ለመረዳት ያስችላል ተብሏል፡፡


በተጨማሪም ንብረቶች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን እና በስራ ላይ ባለ የህንፃና ንብረት አስተዳደር ሕጎች መሠረት ሥራዎች መከናወናቸውን ማረጋገጥ እና በኦዲት ግኝቱ መሠረት ኦዲት ተደራጊ መሥሪያ ቤቶች የእርምት እርምጃ መውሰዳቸውን መከታተል ደግሞ የመመሪያው ዓላማ ነው፡፡


በ12 ገጽ እና በ5 ከፍሎች የተሰናደው የመንግስት ንብረት ኦዲት መመሪያ የኦዲት ተደራጊ መስሪያ ቤት ተግባርና ኃላፊነትን ሲዘረዝር በኦዲት አድራጊ መስሪያ ቤቶች የተገኘውን የኦዲት ግኝት ላይ ተገቢውን የእርምት እርምጃ መውሰድ አለባቸው ይላል፡፡

ይህን ማስተካካል የሚቻለው በማሻሻያ ሃሣቦችና አስተያየቶች መሠረት በደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ባለት 10 የስራ ቀናት ውስጥ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡


ለኦዲት አስፈላጊ የሆኑ ዶክመንቶችን ማቅረብ ፣ለኦዲት አስመርማሪ መመደብ፣ቢሮ እና ግብዓት ማዘጋጀት የኦዲት ተደራጊ መስሪያ ቤት ሀላፊነት ነው፡፡


የንብረት ኦዲት መረጃን የመያዝ፣ የመፍቀድና የመጠበቅ ኃላፊነት በተመለከተ ደግሞ የኦዲት መረጃዎችን ማየት የፈለገ ማንኛውም አካል የመንግስት ንብረት አስተዳደርር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅና የክፍለ ከተማ ንብረት አስተዲደር ጽህፈት ቤት ኃፊን ፍቃድ ማግኘት እንዳለበት በመመሪያው ሰፍሯል፡፡


የፍትህ አካላት የኦዲት ሥራ ሪፖርቶችን ማየት ወይም መጠቀም ቢፈልጉ ግን መረጃው በህግ ገደብ ካልተጣለበት በስተቀር ሰነዱን የንብረት ኦዲት ኃላፊው መስጠት አለበት ይላል መመሪያው፡፡


የንብረት ኦዲት ቋሚ ሰነዶችም ቢያንስ ለ10 ዓመታት ተጠብቀው መቆየት እንዳለባቸውም ተጠቅሷል፡፡

የኦዲት ሥርዓት ወሰን እና የጊዜ ገደብ በተመለከተ ደግሞ የሚያከናውነው የንብረት ኦዲት በዓለም አቀፍ የውስጥ ኦዲት ደረጃዎች መሠረት ተዓማኒነቱ በተጠበቀና በስጋት ላይ በተመሠረተ አቀራረብ መከናወን አለበት በመመሪያው መሰረት፡፡


በተጨማሪም የኦዲት ዘዴው እንድ ንብረቱ ዓይነት፣ ሥጋትና ብዛት ተለይቶ ሊከናውን ይችላል፡፡


በዚህም መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ውንም ስጋት ባለባቸው ዘርፎች ላይ የ100 በመቶ ዝርዝር ኦዲት እንደሚደረግ፣በመካከለኛ የቢሮ እቃዎች ላይ ከ60 እስከ 70 በመቶ የናሙና ኦዲት እንደሚደረግ እና ከፍተኛ ብዛትና አነስተኛ ዋጋ ባላቸው አላቂ ዕቃዎች ላይ ከ40 እስከ 50 በመቶ የናሙና ኦዲት ይደረጋል፡፡


በኦዲት አድራጊው መስሪያቤት የሚደረገው መደበኛ ኦዲት ወደ ኋላ መሄድ የሚችለው እስከ 2 የበጀት ዓመታት እንደሆነ ተዘርዝሯል፡፡


ነገር ግን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን የሚያሳይ ጠንካራ ፍንጭ ወይም ጥፋትን የማመን ሁኔታዎች ሲኖሩ የኦዲት ምርመራው እስከ 10 ዓመት ወደኋላ ተመልሶ ሊከናወን ይችላል ብሏል የመንግስት ንብረት ኦዲት መመሪያው፡፡


የንብረት ኦዲተሮች በስራቸው አጋጣሚ የሚያገኙትን መረጃ ምስጢርና ደህንነት መጠበቅም ግዴታ አለባቸው፡፡


ያሬድ እንዳሻው

1 Comment


镇华 莫
镇华 莫
Jul 03

The post about Addis Ababa’s audit progress shows how important clear information is for citizens. Just like a good Last War guide helps players plan their moves, reliable reports help communities stay informed and safe.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page