top of page

የአካቶ ትምህርት ዘርፉ ከሚጠይቀው ሰፊ ፋይናንስ አቅም እና ካለው የባለሙያ እጥረት አኳያ

  • Feb 24
  • 1 min read

የካቲት 17/2018

 

ትምህርት ለሁሉም ሰው እኩል ማዳረስ የትምህርት ሚኒስቴር ቀዳሚ ግቤ ነው በሚል በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ ይታያል ፡፡

 

በተለይም አካል ጉዳት እና ሌሎች ጉዳቶች ላለባቸው ሰዎች ከሌላው እኩል የትምህርት ተጠቃሚ ማድረግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ህግ ቀርፃ ሰው አሰልጥና ለመስራት ደፋ ቀና እያለች ነው፡፡

 

በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት ትምህርት ቤቶች የአካል ጉዳት ያለባቸው ህፃናት ከእድሜ እኩዮቻቸው እኩል ትምህርት እንዲያገኙ ማድረግ አለባቸው በሚል የአካቶ ትምህርት ትግበራ እንዲተገበር እያደረገ ነው፡፡

 

ነገር ግን ዘርፉ ከሚጠይቀው ሰፊ ፋይናንስ አቅም እና ካለው የባለሙያ እጥረት አኳያ አተገባበሩ ፈታኝ እያደረገው መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣል፡፡

 

ሸገር ራዲዮ ያነጋገራቸው የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችም የሚያነሱት ይህንኑ ነው፡፡

 

በልዩ ፍላጎት የሰለጠነ በቂ የመምህራን ቁጥር አለመኖር፣ የትምህርት ቁሳቁስ እጥረት፣ የመሰረተ ልማት ምቹ አለመሆን እና ሌሎች ችግሮች እንዳሉባቸው ተማሪዎቹ ያነሳሉ፡፡

 

ትምህርት ሚኒስቴርም በበኩሉ ችግሮች እንዳሉ አምናለሁ የሚታዩ ክፍተቶችንም ለማጥበብ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….  

ፋሲካ ሙሉወርቅ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page