የአካል ጉዳተኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ርግበ ገብረ-ሐዋሪያ የተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ።
- Jun 10
- 1 min read
ሰኔ 3/2018
የአካል ጉዳተኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ርግበ ገብረ-ሐዋሪያ የተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተጓደሉ አባላት ምትክ ባካሄደው ምርጫ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሚቴው አባል መሆን ችላለች።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ህፃናት፣አካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር የነበሩት ርግበ ገብረ-ሐዋሪያ ትናንት በኒውዮርክ በተካሄደው የሀገራት ሚስጥራዊ ምርጫ አሸናፊ ሆነዋል።
ከአባል ሀገራቱ የ133ቱን ድምፅ በማግኘት ከአፍሪካ ቀዳሚ ከዓለም ከተወዳደሩት አራተኛውን ከፍተኛ ድምፅ ማግኘታቸው ተነግሯል።

የተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት ኮሚቴ፣በዓለም ዙሪያ የሀገራትን ከአካል ጉዳተኞች መብት ጋር የተገናኘ ደረጃ የሚፈትሽና የሚከታተል ነው ተብሏል።
በየጊዜው በመገናኘትም ይህንኑ የክትትልና ቁጥጥር ስራን እንደሚሰራ ተነግሯል።
የኮሚቴው አባል ሆነው የተመረጡት ርግበ ገብረ-ሐዋሪያ ይህ እድል ለኢትዮጵያ ሲሰጥ የመጀመሪያ መሆኑን ተናግረው ለአፍሪካም፣ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞችም ድምፃቸውን ለማሰማት ትልቅ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
ዘጠኝ አባላት ያለው ኮሚቴው የአራት ዓመት የስራ ዘመን እንደሚኖረውም ተነግሯል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i





Comments