የባህርማዶ ወሬዎች - ሐምሌ 9 2017
- Jul 16, 2025
- 1 min read

ዩክሬይን
የዩክሬይኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴኒስ ሺማይሐል የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ፡፡
ቀደምሲል የዩክሬይኑ ፕሬዘዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ተቀዳሚ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የቆዩትን ዩሊያ ሲቪሪዴንኮን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ማጨታቸውን እወቁልኝ እንዳሉ ሬውተርስ ፅፏል፡፡
የሺማይሐልየስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባት በዚህ ሳምንት በዩክሬይን መንግስት ውስጥ ይከናወናል የተባለው ሹም ሽር አካል ነው ተብሏል፡፡
የሹም ሽሩ ለአገሪቱ ፓርላማ ውሳኔ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው የቆዩት ሩስቴም ኡሜሮቭ በአሜሪካ የዩክሬይን አምባሳደር እንደሚደረጉ ተነግሯል፡፡
ዜሌንስኪ ለውጡ በእጅጉ አስፈላያችን ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

በሶሪያ መንግስት ሀይሎች ላይ ድብደባ የተፈፀመው የድሩዝ እምነት ተከታይ ማህበረሰቦች መኖሪያ ወደሆነችው ስዌይዳ ከተማ ለመዝለቅ በሞከሩበት ወቅት አንደሆነ የእስራኤል የጦር ሹሞች መናገራቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ የከተማዋ ድሩዝ ማህበረሰብ አባሎች ከበድዊን ጎሳዎች ጋር ሲጋጩ መሰንበታቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
የእስራኤል መንግስት የሶሪያ ጦር በድሩዞቹ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሰ ነው ሲል ይከሳል፡፡ የሶሪያ መንግስት የታጠቁ ወታደሮቼን ወደ ስዌይዳ የላኩት በዚያ በተፋላሚ ወገኖቹ መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ለማስከበር አልሜ ነው በማለት ላይ ይገኛል፡፡ በእስራኤል ድብደባ በሶሪያ መንግስት ሀይሎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት በዝርዝር የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

ኒውዮርክ
የተባበሩትመንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለእስራኤል እና ፍልስጤማውያን ነባር ችግር ሁነኛው መፍትሄ የሁለት መንግስታት መሳ ለመሳ መኖር ነው አሉ፡፡
ጉዳዩ የሁለት መንግስታት መፍትሄ በሚል ለበርካታ አመታት ሲነሳ የቆየ መሆኑን አናዶሉ አስታውሷል፡፡
የሁለት መንግስታት መፍትሄ ፍልስጤማውያንም የነፃ አገር ባለቤቶች እንዲሆኑ የሚጠይቅ ሀሳብ ነው፡፡
ጉቴሬዝ በጋዛ የተኩስ አቁም ብቻ መደረሱ በቂ አይሆንም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት የእስራኤል የፖለቲካ ሹሞች የሁለት መንግስታትን የመፍትሄ ሀሳብ ወደ ጎን እያሉት መምጣታቸው ይነገራል፡፡
እስራኤል በአሁኑ ወቅት በጋዛ የምታካሂደውን የጦር ዘመቻ እያሰፋችው ነው ይባላል፡፡

ኮንጎ ኪንሻሳ
በኮንጎ ኪንሻሳ ከተከሰተ የቆየው የኮሌራ ወረርሽኝ በጣሙን እየተስፋፋ ነው ተባለ፡፡
ወረርሽኙ ከመንፈቅ በላይ ማስቆጠሩን ዘ ኢስት አፍሪካን ፅፏል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ኮሌራ አገሪቱ ካሏት 37 ግዛቶች በ17ቱ በጣሙን እየተዛመተ መሆኑን የጤና ሚኒስትሩ ሮጀር ካምባ ተናግረዋል፡፡
ወረርሽኙ አሁን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
ትሾፖ የተሰኘው ግዛት ደግሞ የኮሌራ ወረረሽኙ በእጅጉ የበረታበት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
በበሽታው ከሚያዙት መካከል የ3 በመቶዎቹ ሕይወት እያለፈ መሆኑን በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
የጎርፍ መደጋገም እና የንጹህ ውሃ እጦት ወረርሽኙን ካባባሱ ምክንያቶች መካከል ናቸው ተብሏል፡፡
የኔነህ ከበደ
_edited.jpg)



For anyone interested in testing reaction speed or simply looking for a quick and entertaining challenge, trying a Spacebar Clicker Test can be an enjoyable option. It shows that creative game design does not always require advanced technology. Sometimes, a simple idea executed well is enough to create an experience that players remember and return to again and again.
Mấy hôm nay thời tiết Bắc Ninh thay đổi khá nhanh, sáng nắng nóng nhưng chiều tối lại dễ xuất hiện mưa dông. Mình thường vào xem dự báo thời tiết Bắc Ninh trên website này trước khi ra ngoài. Thông tin nhiệt độ hiện tại, độ ẩm, sức gió, tia UV và cảm giác nhiệt độ thực tế được cập nhật khá đầy đủ. Đặc biệt còn có dự báo chi tiết theo từng xã, phường nên rất tiện để chủ động sắp xếp công việc.
Không cần đợi bản tin thời tiết trên TV, giờ chỉ cần mở website là mình biết ngay thời tiết Tp Hồ Chí Minh trong những ngày tới. Trang cập nhật dữ liệu liên tục cho 34 tỉnh thành trên cả nước, riêng TP.HCM có đầy đủ các chỉ số cần thiết để theo dõi thời tiết và chủ động hơn trong mọi kế hoạch cá nhân.
This Slither io style often blends reality and imagination, allowing the writer to preserve mood and emotion rather than strict factual reporting.