የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚያጋጥማቸውን የፀጥታ እና ተያያዥ ችግሮች እንዲፈቱ በመደረጉ የሚያመርቱ የምርት መጠን ጨምሯል ሲል የማዕድን ሚኒስቴር ተናግረ
- sheger1021fm
- May 30, 2024
- 1 min read
የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚያጋጥማቸውን የፀጥታ እና ተያያዥ ችግሮች እንዲፈቱ በመደረጉ የሚያመርቱ የምርት መጠን ጨምሯል ሲል የማዕድን ሚኒስቴር ተናግረ፡፡
የአገሪቱን የሲሚንቶ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድገው የተነገረለት የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ግፋ ቢል በሁለት ወር ውስጥ ምርት እንደሚጀምር የማዕድን ሚኒስትሩ ሀብታሙ ተገኝ ለህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት አስረድተዋል፡፡
ምርት አቁሞ የነበረው የምሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ዳግም ስራ መጀመሩ እንዲሁም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ችግር የሆነባቸው የፀጥታ ችግር እንዲፈታ በመሰራቱ የሲሚንቶ ምርት ጨምሯል ያሉት ሚኒስትር ሀብታሙ በዚህም ባለፉት 9 ወራት 5.4 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ ተመርቷል ብለዋል፡፡
ይህም የእቅዱን 85 በመቶ ነው፣ ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ22 ብልጫ አሳይቷል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ…
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments