ሰኔ 20፣2015
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከሰሞኑ የዋግነር አመፅ የማነሳሳት ሙከራ ጀርባ የምዕራባዊያን እጅ ስለመኖሩ እየመረመርን ነው አሉ፡፡
ላቭሮቭ በዋግነር የተነሳው አመፅ እንደሚሳካ በአሜሪካ የደህንነት መስሪያ ቤቶች አስቀድሞ ተስፋ ተደርጎ እንደነበር ማንሳታቸውን አል አረቢያ ፅፏል፡፡
እንደውም የአሜሪካ የደህንነት ሹሞች ከዋግነሮች አመፅ መቀስቀስ አስቀድሞ ምልክቶችን አይተናል ማለታቸውን ላቭሮቭ ተናግረዋል፡፡
አመጹ በ24 ሰዓታት ጊዜ መክኗል፡፡
በጉዳዩ የምዕራባዊያን እጅ እንዳለበት ለማወቅ በሩሲያ የደህንነት መስሪያ ቤት እየተመረመረ መሆኑን ላቭሮቭ ተናግረዋል፡፡
የስልጡን ቅጥረኛ ወታደሮች አቅራቢው የዋግነር ኩባንያ የበላይ እና የአመፁ መሪ ውጥናቸውን ትተው ወደ ቤላሩስ ማምራታቸው ታውቋል፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Kommentarer