የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጠው ‘’ያንጎ’’ የስራ ላይ ደህነት ለማስጠበቅ በብርቱ እየሰራሁ ነው አለ
- sheger1021fm
- May 14, 2024
- 1 min read
የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጠው ‘’ያንጎ’’ የስራ ላይ ደህነት ለማስጠበቅ በብርቱ እየሰራሁ ነው አለ፡፡
ለዚህም እንዲረዳኝ የዲጂታል ስርዓት እየተጠቀምኩ ነው ብሏል፡፡
ይህም የአሽከርካሪዎችና የደንበኞችን ደህንነት እንዲጠበቅ ይረዳል መባሉን ሰምተናል፡፡
ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሜትር ታክሲ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 7 ወራትን አስቆጥሯል፡፡
በአጋርነት ለመስራት ወደ ያንጎ ለሚመጡት አካላትመም ድርጅቱ ስልጠና እንደሚሰጥም የድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ይቅና አለም አበበ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Comments