top of page

ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡

  • Jun 29
  • 1 min read

ሰኔ 22/2018

 

ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡ 

 

የከተማዋ ትምህርት ቢሮ በሰጠው መግለጫ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች 95 ነጥብ 8 በመቶ፤ ከግል ት/ቤት ተማሪዎች ደግሞ ከ99 በመቶ በላዩ ማለፋቸውን ተናግሯል፡፡ 

 

የማለፊያ ነጥቡ 50 በመቶና ከዚያ በላይ ሲሆን 1 ሺህ 313 ተማሪዎች ከ90 በመቶ በላይ አግኝተዋል፡፡ 

 

በትምህርት ቢሮ ማህበራዊ ትስስር ገፅ የተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንክ ተማሪዎች ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ 

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ......

 

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page