ሐምሌ 4፣ 2016 - ዕርዳታ የሚፈልጉ ሰዎችን ቁጥር አጋነው የሚያቀርቡ ግለሰቦችን ተጠያቂ የሚያደርግ ህግ እየተዘጋጀ ነው ተባለ
- sheger1021fm
- Jul 11, 2024
- 1 min read
ተፈጥሯዊ እና ሠው ሰራሽ በሆኑ ምክንያቶች ዕርዳታ የሚፈልጉ ሰዎችን ቁጥር አጋነው የሚያቀርቡ እና ዕርዳታን ለማይገባቸው ሰዎች የሚያከፋፍሉ ግለሰቦችን ተጠያቂ የሚያደርግ ህግ እየተዘጋጀ ነው ተባለ።
ተፈጥሯዊ እና ሠው ሰራሽ በሆኑ ምክንያቶች ዕርዳታ ለሚፈልጉ ሰዎች በሚቀርብ ድጋፍ ላይ ከሚገጥሙ ችግሮች አንዱ፤ የቁጥር መጋነን እንደሆነ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ይናገራል።
በተለይ ከኮሚሽኑ ድጋፍ የሚፈልጉ ክልሎች የተረጂዎችን ቁጥር እያጋነኑ እንደሚያቀርቡ ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት ነግሮናል።
የተላከን ዕርዳታ ለማይገባቸው ሰዎች የሚያከፋፍሉ እና ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ ግለሰቦች እንደሚገጥሙም ያነሳል።
በአገር አቀፍ ደረጃ ለተዘጋጀው የአደጋ ስጋት አመራር ፖሊሲ ማስፈጸሚያ የተቀረፀው ረቂቅ አዋጅ በእንዲህ አይነት ተግባር የሚሳተፉ ሰዎችን የሚቀጣ ድንጋጌ እንዳካተተ ሠምተናል።
አቶ አታለለ አቦሃይ በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ሲሆኑ የቅጣት ድንጋጌ በረቂቅ አዋጁ መካተት ክልሎች በሃላፊነት ስሜት የድጋፍ ፈላጊዎችን ቁጥር እንዲያሳውቁ፤ በስራው የሚሳተፉ ሰዎችም ለሚገባው ሰው ብቻ ዕርዳታውን እንዲያከፋፍሉ ይረዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ አታለለ ተናግረዋል።
ንጋቱ ረጋሳ
Kommentare