ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ተሰጥተው በጊዜያቸው ያልተመለሱ የብድር እዳዎችን እያሰመለሰ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ተናገረ፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት ዉስጥም 150 ሚሊዮን ብር የብድር እዳ ተመላሽ ተደርጓል ተብሏል፡፡
በጥናት የተለዩ ከ100,000 በላይ ስራ አጥ ወጣቶች በአሁን ሰዓት በክልሉ መኖራቸውንም ሰምተናል፡፡
አሁን ከተመለሰው ውጪ ለዓመታት ያልተመለሱ የብድር እዳዎች ስላሉ እነሱንም ጭምር አስመለሼ የተመለሰው ብርም እነዚህን ስራ አጥ ወጣቶች አደራጅቼ ስራ እንዲሰሩበት አደርጋለሁ ሲል ክልሉ ለሸገር ተናግሯል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments