top of page

ከጎርጎርሳውያኑ ከ2024 ጀምሮ ኢትዮጵያ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ተብሏል።

  • Mar 5
  • 2 min read

የካቲት 26/2018

 

ከጎርጎርሳውያኑ ከ2024 ጀምሮ ኢትዮጵያ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከአፍሪካ ሁለተኛ ፤ ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ተብሏል።

 

በቀጣይ ወር በአዲስ አበባ በሚዘጋጀው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ብቻ ከ2.4 ቢሊየን ዶላር በላይ ግምት ያለው የኢንቨስትመንት ስምምነት ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተነግሯል።

 

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የገንዘብ ሚኒስቴር ፎረሙን አስመልክተው ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

 

ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት እና ሌሎች ዘርፎችን የሚደግፉ ከ123 በላይ አዳዲስ ህጎችን ባለፉት ሰባት ዓመታት አውጥታለች ተብሏል።

 

ማሻሻያ የተደረገባቸው ህጎች ከተጨመሩበት ደግሞ ቁጥሩ ከ198 እንደሚልቅ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ዶክተር ዘለቀ ተመስገን ተናግረዋል።

 

ከወጡ ህጎች አንዳንዶቹ ለውጪ ባለሃብቶች ዝግ የነበሩ ዘርፎች እንዲከፈቱ ያስቻሉ ናቸው ብለዋል።

እነዚህን ጨምሮ በመንግስት በከል የተወሰዱ የተለያዩ እርምጃዎች ኢትዮጵያን በተሻለ መልኩ  የኢንቨስትመንት መዳረሻ እያደረጓት እንደሚገኙ ጠቅስዋል።

 

ከጎርጎርሳውያኑ ከ2024 ጀምሮ ኢትዮጵያ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ነው ያሉት። 

 

በኢትዮጵያ ሲሰሩ የቆዩ እና በተለያየ ምክንያት ለቀው የሄዱ ባለሃብቶች እንዳሉ በተለያየ መንገድ ሲነገር ይሰማል ፤ ይህ ከኮሚሽኑ መረጃ ጋር እንዴት ይጣጣማል? በሚል የተጠየቁት ኮሚሽነሩ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

 

ኢትዮጵያ አራተኛውን የኢንቨስትመንት ፎረም መጋቢት 17 እና 18 /2018 በአዲስ አበባ እንደምታሰተናግድም ተነግሯል።

 

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር እና  አጋር አካላት በትብብር የሚያዘጋጁት ፎረም እንደሆነ ነው የሰማነው።

 

በፎረሙ ላይ ከ2.4 ቢሊየን ዶላር በላይ ግምት ያለው የኢንቨስትመንት ስምምነት ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኮሚሽነር ዘለቀ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡

 

ለኢንቨስትመንት ፍሰቱ ፈተና የሆኑ አንዳንድ የፀጥታ ችግሮች በተለያዩ አካባቢው እንዳሉ ይታወቃል ያሉት፤ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው መንግስት እነዚህም ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

 

በፎረሙ ላይ ከ800 በላይ አለም አቀፍ ባለሃብቶች ፤ የንግድ መሪዎች ፤ ፖሊሲ አውጪዎች የልማት አጋሮች ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል፡፡

 

ንጋቱ ረጋሣ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page