ከአዲስ አበባ ከተማ መሬት 52 በመቶው ለመንገድ፤ ለወንዝ ዳርቻ እና ለአረንጓዴ ልማት የተያዘ ነው ተብሏል።
- Mar 16
- 1 min read
መጋቢት 7/2018
ከአዲስ አበባ ከተማ መሬት 52 በመቶው ለመንገድ፤ ለወንዝ ዳርቻ እና ለአረንጓዴ ልማት የተያዘ ነው ተብሏል።
ለመኖሪያ እንዲሁም ለመስሪና ማምረቻ ሊውል የሚችለው የከተማዋ መሬት 48 በመቶ ብቻ እንደሆነ የከተማ ልማት ባለሞያው አቶ ሢሣይ ዘነበ ይናገራሉ።
ፍላጎቱን ከአቅርቦቱ ጋር እንዳይጣጣም ያደረገው አንዱ ምክንያትም ይኸው እንደሆነ ባለሞያው ይጠቅሳሉ።
በየጊዜው የሚጨምረው የህዝብ ቁጥር እና ወደ ከተማዋ የሚደረግ ፍልሰት ነገሩን ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎታልም ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ይህን እጥረት ያለበት ሃብት ለግለሰቦች ከሚያስተላልፍባቸው መንገዶች አንዱ ሊዝ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ሢሣይ የዚህ ክፍያ ግን ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህ ከፍተኛ ክፍያ ደግሞ ግለሰቡ መሬቱ ላይ ገንዘቡን ስለሚጨርስ ለግንባታ የሚተርፈው ነገር እንዳይኖር ያደርጋል ብለዋል።
ሆንግ ኮንግ እና አመስተርዳምን የመሰሉ ከተሞችም መሬት በሊዝ ለግለሰቦች እንዲተላለፈ ያደርጋሉ የሚሉት ባለሞያው አሰራሩ ግን ጥብቅ ቁጥጥር ያለበት እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በሌላ በኩል ከተሞቹ ክፍያ የሚጠይቁት ግንባታው ተከናውኖ አካባቢው ከለማ በኋላ እንደሆነ ተናግረዋል።
ክፍያ የሚጠይቁት ግን ግንባታ ከተከናወነ እና ልማት ከተሰራ በኋላ እንደሆነ ተናግረዋል።
እንደ እኛ ለመሬቱ ሳይሆን የሚያስከፍሉት ለመጣው ልማት ነው ብለዋል፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ በብዙ አካባቢዎች መሬት ለማግኘት ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚጠይቅ የተናገሩት ባለሞያው ይህም ዋጋውን ከፍ የሚያደርግ ሌላ ምክንያት ነው ይላሉ።
የመሬት ፍላጎት ከአካባቢ ጋርም የተገናኘ እንደሆነ ባለሞያው አቶ ሢሣይ ተናግረዋል።
ፒያሣ ላይ ሞል ልገንባ ብሎ መሬት የጠየቀ ባለሃብት ረፒ ላይ ቦታ ቢሰጠው አይቀበልም ነው ያሉት።
ለዚህ መፍትሄው የሊዝ ጨረታዎችን ዓይነት ማብዛት እንደሆነ ጠቅሰዋል።
አስራ ሶስት በሚሆኑ የኢትዮጵያ ከተሞች ላይ በተደረገ ጥናት የሁሉም ማስተር ፕላን ወደ ጎን መስፋትን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ መረጋገጡን አቶ ሢሣይ ተናግረዋል።
አዲስ አበባም ከእነዚህ ከተሞች መካከል አንዷ ናት ያሉት ባለሞያው ማስፋፊያው ግን አስቀድሞ ታሳቢ ሊያደርጋቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዳሉ አመልክተዋል።
በየጊዜው የሚወጡ ህጎችን እየፈተሹ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባም አስፈላጊ እንደሆነ አቶ ሢሣይ ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ንጋቱ ረጋሣ





Comments