ከአንድ ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያዊያን በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በተለያዩ ስራዎች ተሰማርተው እንደሚገኙ ይነገራል።
- May 25
- 1 min read
ግንቦት 17/2018
የእቃ አስተላላፊነት ዘርፍን ለውጪ ባለሀብቶች ሙሉ በሙሉ ክፍት አንዲሆን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ወሰነ፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ የእቃ አስተላላፊነት ዘርፍን ለውጭ ባለሃብቶች ተሳትፎ ክፍት ለማድረግ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል፡፡
ቀደም ሲል የውጭ ባለሀብቶች የዕቃ አስተላላፊነት የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች የቅንጅት ኢንቨስትመንት የተከለለ ሲሆን የውጭ ባለሃብቶች የካፒታል የሽርክና ተሳትፎም በ49 በመቶ ተገድቦ መቆየቱ ተነስቷል።

ከዚህም የተነሳ በዘርፉ የሚፈለገውን አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ክፍተት ፈጥሮ የቆየ ሲሆን የቦርዱ ውሳኔም ይህን እና መሰል ችግሮችን የሚቀርፍ እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በዘርፉ የተሰማሩ ነባር ባለሃብቶችንም ሆነ አዲስ ወደ ዘርፉ ለሚገቡት ባለሃብቶች በሎጂስትክስ ዘርፉ ላይ ተጨማሪ እምነት እንዲያሳድሩም የሚያግዝ ነው ተብሏል።
በውሳኔው መሰረት ዘርፉን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ማድረግ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት፣ አገራዊ የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት እንዲሁም የአገር ውስጥ ተዋናዮች አቅማቸውን አሳድገው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ስለመባሉ ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች እየሰራ ሲሆን ይህ ውሳኔም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በማህበራዊ ትስስር ገፅ አዉርቷል።
ገዛ ጌታሁን





I bookmarked this name generator after using it for a couple of projects. It’s useful when you need fresh naming ideas without spending hours brainstorming.