top of page

መጋቢት 3፣2016 - ከህዝብ አቤቱታ እና ቅሬታ የሚቀበልበትን አጭር የስልክ መስመር በአዲስ በመቀየር ስራ መጀመሩን እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

ከህዝብ አቤቱታ እና ቅሬታ የሚቀበልበትን አጭር የስልክ መስመር በአዲስ በመቀየር ስራ መጀመሩንየኢትዮጵያ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡


አዲሱ ጥቆማ የሚቀበልበት አጭር የስልክ መስመር ቁጥርም 9503 ነው ተብሏል፡፡


ከዚህ በፊት ከህዝብ አቤቱታ እና ቅሬታ ይቀበልበት የነበረው አጭር የስልክ መስመር ስራ በማቆሙ ይደርሰው ከነበረው አቤቱታ በአንድ አራተኛ ቀንሶ እንደነበረም ተቋሙ አስታውሷል፡፡


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments


bottom of page