እንደ ጣና ያሉ ሀይቆችና የውሃ አካላት ላይ ተንሰራፍቶ ከሚገኘው የእምቦጭ አረም የነዳጅ ምርቶችን ለማምረት ይሰራል ከተባለ ከአምስት አመት በላይ ሆኖታል።
- Aug 5
- 1 min read
ሐምሌ 29 2018
እንደ ጣና ያሉ ሀይቆችና የውሃ አካላት ላይ ተንሰራፍቶ ከሚገኘው የእምቦጭ አረም የነዳጅ ምርቶችን ለማምረት ይሰራል ከተባለ ከአምስት አመት በላይ ሆኖታል።
ይተገበራል በተባለው ፕሮጀክትም ነጭ ጋዝ፣ ቤንዚን ፣ኪሮሲን፣ የአውሮፕላን ነዳጅ እና ሚቴን ማምረት የሚለው ይገኝበታል ።
ተረፈ ምርቱ ከነዳጅ ምርቱም ጎን ለጎን ለከሰል እና ለእደጥበብ ውጤቶችም ይውላል መባሉ ይታወሳል።
ከእምቦጭ ነዳጅም ሆነ ሌሎች ምርቶችን ለማምረት ከውጪ ሀገራት ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት እንደነበረም መረጃዎች ያሳያሉ።
ለመሆኑ ነዳጅን ከእምቦጭ አረም ለማግኘት ተይዞ የነበረው እቅድ ከምን ደረሰ ?
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴርን ጠይቀናል።
አቶ ወንድወሰን አበጀ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢኮ ሃይድሮሎጂ ፕሮጀክትና የመጤ አረሞች ማስወገድ እና መከላከል አስተባባሪ ናቸው።
ከእምቦጭ አረም ነዳጅ ለማግኘት የታሰበው እቅድ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም ብለዋል።
እቅዱን ለመተግበር ከሞሮኮ ጋር ስምምነት ላይ የተደረሰ ቢሆንም ከሞሮኮ በኩል ሲያስተባብሩ የነበሩ አካላት በመቀያየራቸው ክፍተት በመፈጠሩ እና በመቀዛቀዙ እቅዱን ወደ መሬት ለማውረድ እንቅፋት መሆኑን ነግረውናል።
አክለውም በእኛ በኩል ምርቱ እንዲጀመር ብንፈልግም ከሞሮኮ ጋር የማምረት እቅዱን የተስማማነው በእነርሱ መልካም ፈቃድ በመሆኑ ማስገደድ አልቻልንም ብለዋል ።
ከእምቦጭ አረም የነዳጅ ምርቶችን ለማምረት የታቀደው ፕሮጀክት ወደ ተግባር ባይገባም እንደገና
ለመቀጠል እና ወደስራ ለመግባት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል እቅድ ተይዞ እየተሰራበት እንደሆነ እና ማምረት እንደሚጀመርም አቶ ወንድወሰን ነግረውናል።
በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም የእምቦጭ አረምን ወደ ከሰል እና ወደ ተለያዩ ምርቶች እየቀየሩ ሲጠቀሙ የነበሩ ማህበረሰቦች እንዳሉ አስታውሰው አሁን ላይ ግን በስፋት እየተሰራበት አይደልም ብለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
ፍቅሩ አምባቸው
_edited.jpg)




Comments