top of page

እስራኤል በዌስት ባንክ ጄኒን ከተማ ድብደባ እየፈፀመች ነው


ሰኔ 26፣2015


እስራኤል በዌስት ባንክ ጄኒን ከተማ ድብደባ እየፈፀመች ነው፡:


ዛሬ ማለዳ እስራኤል በጀኒን ከተማ በሚገኘው የፍልስጤማውያን የስደተኞች ሰፈር ላይ በፈፀመችው የአየር ጥቃት በጥቂቱ 3 ሰዎች እንደተገደሉ አናዶሉ ፅፏል፡፡


13 ሰዎች ደግሞ የተለያየ ደረጃ አካላዊ ጉዳት ገጥሟቸዋል ተብሏል፡፡


እስራኤል የጄኒኑ የስደተኞች ሰፈር የአሸባሪዎች ምሽግ ነው ትላለች፡፡


ከአየር ድብደባውም በኋላ የእስራኤል እግረኛ ወታደሮች ወደ ጀኒን የስደተኞች መጠለያ ሰፈሩ እየገፉ ነው ተብሏል፡፡


ፍልስጤማውያን ታጣቂ ቡድኖች ፣ ሐማስ ፣ ኢስላማዊ ጂሃድ እና የፈታህ ንቅናቄ ወታደራዊ ክንፍ ተባብረን እስራኤልን እንፋለማታለን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


በእስራኤል የዌስት ባንክ የሰፈራ ማስፋፊያ የተነሳ ውጥረት እና ግጭት እየተባባሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡



የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page