እስራኤል በኢራን ላይ ድንገተኛ የሚሳኤል ጥቃት መፈፀሟ ተነገረ፡፡
- Feb 28
- 1 min read
የካቲት 21/2018
እስራኤል በኢራን ላይ ድንገተኛ የሚሳኤል ጥቃት መፈፀሟ ተነገረ፡፡
አልጀዚራን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጥቃቱን የተመለከተ መረጃን በሰበር ወሬ ይዘው ቀርበዋል፡፡

እስራኤል በፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት በቴህራን ማዕከላዊ ከተማ የፍንዳታ ድምፅ መሰማቱ ተሰምቷል፡፡
ፋርስ የወሬ ምንጭ እንደዘገበው በማዕከላዊ ቴህራን ዩኒቨርስቲ ጎዳና እና ጃዋሆሪ በተባሉት ማዕከላዊ የቴህራን ክፍል ተደጋጋሚ የሚሳኤል ጥቃት ተሰንዝሯል፡፡
የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እርምጃው እራስን ከጥቃት የመጠበቅና ቀርቦ የመከላከል ነው ብለውታል፡፡
አሶሼትድ ፕሬስ የመረጃ ምንጭ ደግሞ የእስራኤል ጥቃት የተፈፀመው በኢራን ዋና ከተማ በከፍተኛ መንፈሳዊው መሪው አያቶ አሊ ካሚኒ ቢሮ አካባቢ ነው ብሏል፡፡
ዝርዝር መረጃ ግን እስካሁን አልወጣም፡፡





Comments