ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የአገልግሎት ታሪፍ ማሻሻሉ ተሰማ።
- sheger1021fm
- Dec 29, 2025
- 1 min read
ታህሳስ 20/2018
ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የአገልግሎት ታሪፍ ማሻሻሉ ተሰማ።
ከባንያው በተለያዩ አገልግሎቶች ላይ ያደረገው አማካይ የ ዋጋ ማሻሻያ የ23% በመቶ እንደሆነ ሰምተናል።
ኢትዮ ቴሌኮም ይህን የታሪፍ አገልግሎት ማሻሻያ ያደረኩት፤ ተለዋዋጭ የ ማክሮ ኢኮኖሚ ፤ የካፒታል እና የስራ ማስኬጃ ወጭዎች ከፍ በማለቱ ነው ብሏል።
ከዚህም ባለፈ ኩባንያው፤ የአገልግሎት ጥራትን ለማስጠበቅ የታሪፍ ማሻሻያ አድርጌያለሁ ብሏል።
በዚህም መሰረት የ ዋጋ ማሻሻያ ከተደረገባቸው አማካይ 23 በመቶ ውስጥ የቴሌብር ልዩ ስጦታ ጥቅል የ10% ቅናሽ ወደ 20% ከፍ ብሏል።

ኩባንያው ካሉት አብዛኛው ጥቅሎች ላይ 38 የተለያዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አላደረኩም ብሏል።
ከዚህ ውስጥም የ1 ብር፣ የ2 ብር፣ የ5 ብር እና የ1 ሰዓት ጥቅሎች ባሉበት እንዲቀጥሉ ወስኛለሁ ማለቱን ከኩባንያው ሰምተናል።
በተመሳሳይ የኢትዮዽያን የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ሁለተኛ አቅራቢ ሆኖ የተቀላቀለው ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉ ይታወቃል።
ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ ይህንን ጭማሪ ያደረገው በተመሳሳይ የኢንቨስትመንት እና የኦፕሬሽናል ወጪዎች ከፍ ማለታቸውን ተከትሎ እንደሆነ ሰምተናል።
ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ በበኩሉ በአገልግሎቶቹ ላይ ከ 20 በመቶ ጀምሮ እንደየደረጃው እስከ 80 በመቶ ጭማሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
ተህቦ ንጉሴ












Comments