ኢትዮጵያ የምታካሄደውን ሀገራዊ ምክክር በተመለከተ መገናኛ ብዙሀን በኃላፊነት ሊሰሩ ይገባል ተባለ፡፡
- Feb 27
- 1 min read
የካቲት 20 2018
ኢትዮጵያ የምታካሄደውን ሀገራዊ ምክክር በተመለከተ መገናኛ ብዙሀን በኃላፊነት ሊሰሩ ይገባል ተባለ፡፡
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በሚከውናቸው ስራዎች አካታችነቱን የጠበቀ እንዲሆንና ሃገራዊ ምክክሩ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ መገናኛ ብዙሃን ብዙ ሃላፊነት አለባቸው ተብሏል፡፡
ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመገናኛ ብዙሃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ትናንት በአዳማ ከተማ ባደረገው ውይይት ነው፡፡

መገናኛ ብዙሃን በተለይ የሀገራዊ ምክሩን ሂደት በተመለከተ የሚከውኗቸው ስራዎች በደንብ የተጠኑ በኋላም ሊያመጡት የሚችለው ጥሩም ይሁን አሉታዊ ተጽዕኖ ተመዝኖ ሙያዊ ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ መሆን አለበት ሲሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሙሃመድ ድሪር ተናግረዋል፡፡
ሚዲያ በሀገር ግንባታ ላይ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ መረጃዎችና መልዕክቶች ጊዜና ሁኔታን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መሆን አለበት ያሉት ደግሞ ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ ናቸው፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚከወናቸው ስራዎች ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያካተተ ስለመሆኑ ሚድያው ማረጋገጥና ክፍተት ካለም መጠየቅ የሚያስችል ኃላፊነት ድረስ ተሰጥቶታል ይህንንም በአግባቡ ሊጠቀምበት ይገባል ሲሉም ዶር ዮናስ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፉት 4 ዓመታት በተለያዩ አካባቢዎች ከከወናቸው የአጀንዳ ማሰባሰብና ሌሎችም ስራዎች 93 በመቶ ማጠናቀቁን ተናግሯል፡፡
ኮሚሽኑ በተጨመረለት የስምንት ወራት ተጨማሪ ጊዜ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments