ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የጥቃቅን፤ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር ፍላጎት ወደ አንድ ትሪሊየን ብር እንደሚጠጋ ተነግሯል።
- Mar 18
- 2 min read
መጋቢት 9/2018
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የጥቃቅን፤ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር ፍላጎት ወደ አንድ ትሪሊየን ብር እንደሚጠጋ ተነግሯል።
ፍላጎታቸው በሀገሪቱ ካለው አጠቃላይ ገንዘብ ትልቁን ድርሻ የሚይዝ እንደሆነ ተጠቅሷል።
ባንኮችን እና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን በማሳመን ይህን ከፍተኛ የሆነ የብድር ፍላጎታቸውን ለማማሏት ኢንተርፕራይዞቹ ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ሚሊየን የሚጠጉ ጥቃቅን፤ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዳሉ የዓለም ባንክ መረጃ ያሳያል።
የእነዚህ ኢንተርፕራይዞች አጠቃላይ የፋይናንስ ፍላጎት አንድ ትሪሊየን ብር እንደሚጠጋ የባንክ ባለሞያ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሃይሌ የባንኩን መረጃ ጠቅሰው ተናግረዋል።
መደበኛ ባልሆነ የንግድ ስራ ከተሰማሩት ጋር ሲደመሩ ደግሞ የፋይናንስ ፍላጎታቸው 2.6 ትሪሊየን ብር ይጠጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ባንኮችና በማክይሮ ፋይናንስ ተቋማት ያለው እንዲሁም በገበያው ውስጥ የተሰራጨውና በየሰዉ ኪስ ያለው ገንዘብ ሲደመር ደግሞ 3.7 ትሪሊየን ብር ነው ብለዋል።
የባንኩ መረጃ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ገንዘብ ዘርፉ እንደሚፈልግ የሚያሳይ እንደሆነ አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል።
ከዚህ ውስን ከሆነው የፋይናንስ አቅርቦት ተጠቃሚ ለመሆን ዘርፉ በተለያዩ መስፈርቶች ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት እንዳለበትም አመልክተዋል።
የመጀመሪያው አቶ ቴዎድሮስ እንደሚሉት ኢንተርፕራይዞቹን የተመለከተ የተሟላ መረጃ ወይም ዳታ ነው።
የተሟላ መረጃ መኖር አበዳሪው ተቋም በኢንተርፕራይዙ ላይ እምነት እንዲያድርበት ያደርጋል ብለዋል።
ከገንዘብ ባሻገር በአይነትም ለጥቃቅን ፤ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጥ ብድር በኢትዮጵያ በስፋት መለመድ እንዳለበት ባለሞያው ያነሳሉ።
የማምረቻ ዕቃዎችን ገዝቶ በመስጠት በሂደት ኢንተርፕራይዞቹ ዕዳውን ከፍለው ንብረቱን የራሳቸው የሚያደርጉበት የሊዝ ፋይናንስ አንዱ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የኢንተርፕራይዞቹ አንቀሳቃሾች በገንዘብ አስተዳደር ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤም መጠናከር እንዳለበት ባለሞያው ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል።
በገንዘብ አስተዳደር ዙሪያ የተሟላ መረጃ ያለው የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽ የፋይናንስ ተቋማትን አሳምኖ ብድር የማግኘት ዕድሉ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።
ከገንዘብ ተቋማት ብድር ማግኘት ላይ በኢንተርፕራይዞቹ መካከልም ሰፋ ያለ ልዩነት እንዳለ ተጠቅሷል።
ከጥቃቅኖቹ ኢንተርፕራይዞቹ ከባንኮች ብድር እያገኙ ያሉት 1 ነጥብ 9 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው ተብሏል።
በአንጻሩ ከፍ ካሉት 35.5 በመቶ የሚሆኑት ከባንክ ብድር እንደሚያገኙ ተነግሯል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
_edited.jpg)




Comments