ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባንኮች ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው ያላቸው ድርሻ ከ5 እስከ 7 በመቶ ነው ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- 7 days ago
- 1 min read
ጥር 26/2018
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባንኮች ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው ያላቸው ድርሻ ከ5 እስከ 7 በመቶ ነው ተባለ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጎረቤት ሀገራት ባንኮች ለሀገራቸው ጠቅላላ ኢኮኖሚ ያላቸው ድርሻ ከዚህ ይበልጣል ለዚህም ምንክያቱ ባንኮቹ አቅማቸው ስለደረጀና የውጪ ባንኮች ስለገቡ ነው ብለዋል፡፡
ባለፉት 30 ዓመታት የኢትዮጵያ ባንኮች ያለውም ውድድር እንዲሰሩ ቢደረግም የታሰበውን ያህል ሀብት መፍጠር አልቻሉም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባንኮችም አቅማቸው ማደርጀት አለባቸው ያሉ ሲሆን የውጪ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት አለባቸው ብለዋል፡፡
ከውጪ የሚመጡ ባንኮች አጠቃላይ መያዝ የሚችሉት 49 በመቶ ድርሻ ብቻ ነው 5 ለውጪ ባንኮች የሚሠጥ ፍቃድ በ5 አመት ውስጥ የሚካሄድ ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባንኮች ባንክ መሆን አለባቸው በየሰፈሩ መከፈት የለባቸውም ጠንካራ ባንክ ለመሆን የሚያስችል አቅም አላቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የባንኮች ቁጥር ከ5 እስከ 10 በቂ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7












Comments