ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልከውን የቡና ምርት በብዙ እጥፍ ሊያሳድጉ የሚችሉ የቡና ዝርያዎች በምርምር ተገኙ፡፡
ሀገሪቱ በ1 ሄክታር ከምታገኘው የቡና ምርት ከ3 እጥፍ የሚበልጡ የቡና ዝርያዎች በምርምር ተገኝተዋል፡፡
ዝርያዎቹ ለፍሬ ሲበቁ አሁን ከአንድ ሄክታር የሚገኘውን 7 ኩንታል ወደ 23 ኩንታል እንደሚያሳድጉትም ሰምተናል፡፡
በጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር የተገኙት ዝርያዎች 5 ሲሆኑ 3ቱ ለቆላማ አካባቢዎች፣ 2ቱ ደግሞ ለደጋማ አካባቢዎች የአየር ንብረት የተመቹ መሆናቸውን የማዕከሉ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ግርማ ሃይለ ሚካኤል ነግረውናል፡፡
Comments