top of page

አቢሲንያ ባንክ የ5ተኛ ዙር የ“እችላለሁ” እና የ“ይጀምሩ፣ ያድሱ፣ ይደጉ-2” የሽያጭ ዘመቻ የሽልማትና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት አከናወነ።

  • May 21
  • 1 min read

ግንቦት 13/2018


አቢሲንያ ባንክ የ5ተኛ ዙር የ“እችላለሁ” እና የ“ይጀምሩ፣ ያድሱ፣ ይደጉ-2” የሽያጭ ዘመቻ የሽልማትና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት አከናወነ።


ባንኩ አዘጋጅቶ የነበረው የሽያጭ ዘመቻ አዳዲስ ደንበኞች ከባንኩ ጋር ሥራ እንዲጀምሩ እና ነባር አነስተኛ ተቀማጭ ያላቸውና በንቃት የማያንቀሳቀሱ ደንበኞች ግንኙነታቸውን እንዲያድሱ እንዲሁም ሁሉም ደንበኞች ከባንኩ ጋር አብረው ይደጉ በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ያካሄድኩት ነው ብሏል።


በዚህም አንድ ዕድለኛን የመኪና ባለቤት ያደረገ ሲሆን በየሁለት ሳምንቱ ደግሞ ሌሎች በርካታ የሽልማት ዓይነቶችን በመሸለም አጠናቋል።



በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8)ን በማስመልከት ባንኩ ለ5ኛ ጊዜ “እችላለሁ" በሚል ከመጋቢት 8 እስከ ሚያዝያ 23 ቀን 2026 ዓ/ም የቆየ ልዩ ሴቶችን የሚያበረታታ መርሐ ግብር ሲያከናውን መቆየቱ ተናግሯል።


በዚህ ዓመታዊ መርሐ ግብር ባንኩ ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ግንባታ ለፋይናንስ አካታችነት እና በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የታለሙ የማኅበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን ከልዩ ልዩ ማበረታቻዎች ጋር አጣምሮ የያዘ ነበር ተብሏል፡፡


በመርሐ ግብሩ ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ ሴት ነጋዴዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ያስተዋወቁበትና የገበያ ትስስር የፈጠሩበት የንግድ ትርዒትና ባዛር መድረክ በወላይታ ሶዶ፣ በጅማ፣ በደሴና በባሕር ዳር ተከናውኗል ተብሏል።


በዚህም ከ5 በላይ ሴት ነጋዴዎችን ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ በማድረ ግ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ምርቶችን በማምረቻ ዋጋ እንዲያገኙ አስችሏል ሲል ባንኩ ተናግሯል።


ለሴት ሥራ ፈጣሪዎች ያለመያዣ የሚቀርብ የብድር ዕድልን አስመልክቶ ባደረግነው ጥሪ ከ1,200 በላይ የንግድ ሐሳቦች ቀርበውልኛል ሲል ባንኩ አስረድቷል፡፡


ከነዚህም ውስጥ መመዘኛውን ላሟሉ 50 ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ሥራቸውን ለማስፋፋት ይረዳቸው ዘንድ ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ያለ ምንም የንብረት ዋስትና በዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ ተመቻችቶላቸዋል ተብሏል።


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page