አቢሲንያ ባንክ ˝እችላለሁ˝ 5ኛ ዙር የ2025 BYD Seagull ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና የሎተሪ እድለኛን ለመለየት የእጣ ማውጠት ስነ ስርዓት አከናወነ፡፡
- Apr 30
- 1 min read
ሚያዝያ 22/2018
አቢሲንያ ባንክ ˝እችላለሁ˝ 5ኛ ዙር የ2025 BYD Seagull ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና የሎተሪ እድለኛን ለመለየት የእጣ ማውጠት ስነ ስርዓት አከናወነ፡፡
ዛሬ በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት መድረክ ከ2.3 ሚሊዮን በላይ የኩፖን ቁጥሮችን መሠረት በማድረግ የ2025 BYD Seagull ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ዕድለኛን ለመለየት የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
አቢሲኒያ ባንክ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (March 8) በማስመልከት፣ “እችላለሁ ” በሚል መሪ ቃል ለ5ኛ ጊዜ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም የሚያጎለብት መርሐ-ግብር ማካሄዱ ይታወሳል፡፡
ባንኩ ባሰናዳው መርሀ ግብር ላይም በደም እጥረት ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ፣ ሀገር አቀፍ የደም ልገሳ ዘመቻ ያከናወነ ሲሆን በዚህም 3,012 ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል ብሏል፡፡
በተጨማሪም በሐዋሳ፣ ጅማ፣ ደሴ እና ባሕርዳር በተካሄዱ የንግድ ትርዒቶች ላይ ከ450 በላይ ሴት ነጋዴዎች መሳተፋቸውን የተናገረው አቢሲኒያ ባንክ ለ150 ሴቶች በፋይናንስ እውቀትና በንግድ አመራር ላይ ተግባራዊ ሥልጠና መስጠቱን ተናግሯል፡፡
1,234 የንግድ ሐሳቦች ተቀብዬ ለተመረጡ 50 ሴቶች እስከ 25 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ያለ መያዣ ብድር ለመስጠት ዝግጅቴን ጨርሻለሁ ያለው ባንኩ በፈጠራ ውድድር የተሳተፉ እንስቶች እስከ 200,000 ብር የሚደርስ ሽልማት ለማግኘት ለይቻለሁ ብሏል፡፡
ባንኩ በተለይ ሴቶችን ማዕከል አድርጎ የሚሰጣቸውን አደይ እና ዛህራ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶችን በተለየ የፈጠራ ሐሳብ በማስተዋወቅ አልያም የንግድ ማስፋፊያ የፈጠራ ሐሳባቸውን 72 እንስቶች በቲክቶክ አጭር ቪዲዮ ሠርተው በመላክ የተሳተፉ ሲሆን፣ በሁለቱም ዘርፎች የተለዩ 6 እንስቶች ከ100,000 - 500,000 ብር የሚደርስ ሽልማት እንዲያገኙ መለየታቸውን ነግሮናል፡፡
በአጠቃላይ በአንድ ወር ተኩል ጊዜ ውስጥ 3.5 ብር ቢሊዮን ተቀማጭ ገንዘብ ተሰብስቧል፤ 95,568 አዲስ ሒሳቦች ደግሞ ተከፍተዋል ያለው አቢሲኒያ ባንክ ከ20,000 በላይ በሚሆኑ ሴት ነጋዴዎች አማካይነትም ከ607 ሺህ በላይ ዲጂታል ግብይቶች ተከናውኗል ብሏል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments