ሰኔ 13፣ 2016 - አሁን አሁን ስራ ላይ እየዋሉ ያሉ የታክስ ህጎች፤ አነስተኛ ገቢ ያለውን ማህበረሰብ የበለጠ እያደኸዩት ነው ተባለ
- sheger1021fm
- Jun 20, 2024
- 1 min read
አሁን አሁን ስራ ላይ እየዋሉ ያሉ የታክስ ህጎች፤ አነስተኛ ገቢ ያለውን ማህበረሰብ የበለጠ እያደኸዩት ነው ተባል።
ይህ የተባለው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ በተደረገ ውይይት ላይ ነው።
እንዲህ አይነት አዋጆች ምክር ቤቱ ሊያፀድቅ አይገባም ሲሉ አባላቱ ተከራክረዋል።
አንድ የምክር ቤት አባል ባነሱት ጥያቄ ‘’ከታክስ ጋር በተያያዘ እየፀደቁ ያሉ አዋጆች ድሀውን ማህበረሰብ የበለጠ እያደኸዩት ነው፤ ሀብታሙን ግን የማይነካ እና የበለጠ የሚጠቅም ነው አሁን የቀረበው የንብረት እረቂቅ አዋጅም ይህንን ያሳያል’’ ብለዋል።
‘’ከዚህ በፊት ምክር ቤቱ ላይ የመንግስት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ስለማይበቃቸው ቢሮ ላይ ለማደር መገደዳቸው መስማታችን ይታወሳል’’ ያሉት የምክር ቤት አባሉ የንብረት ታክስ አዋጁ ይህንን ያባብሰዋል ይላሉ።
Comentários