ነዳጅ ቀሽበው የተገኙ የቦቴ ሾፌሮች በእምነት ማጉደል በህግ መጠየቅ ሲገባቸው የቦቴው ባለቤቶች ባልተሳፍንበት ወንጀል ክልሎች ንብረታችንን ያላግባብ እየወረሱ ነው ሲሉ ባለንብረቶቹ ቅሬታቸውን ተናገሩ::
- Aug 5
- 1 min read
ሐምሌ 29 2018
ነዳጅ ቀሽበው የተገኙ የቦቴ ሾፌሮች በእምነት ማጉደል በህግ መጠየቅ ሲገባቸው የቦቴው ባለቤቶች ባልተሳፍንበት ወንጀል ክልሎች ንብረታችንን ያላግባብ እየወረሱ ነው ሲሉ ባለንብረቶቹ ቅሬታቸውን ተናገሩ::

የተወረሰውን ነዳጅም ያላግባብ እንድንከፍል በክልሎች እየተጠየቅን ነው ይላሉ፡፡
በሾፌሮች የሚፈፀም ነዳጅ ቅሸባ ተገቢ ያልሆነ ሌብነት ነው የሚሉት ባለንብረቶች ተጠያቂ መሆን አለባቸውም ይላሉ፡፡
አንዳንድ ክልሎች ግን መንግስት ያወጣውን ህግ ሽረው ንብረታችንን በመውረሳቸው እየተቸገርን ነው ሲሉ ባለንብረቶቹ አማረዋል፡፡
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን በበኩሉ የነዳጅ ጉዳይ በአንድ መስሪያ ቤት ብቻ የሚመራ እንዳልሆነና ቅሸባን በተመለከተ ችግሩንም ለመከላከል በጋራ እንደሚሠራ ተናግሯል::
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....
ማርታ በቀለ
_edited.jpg)

Comments