top of page

ነሐሴ 9፣2016 - የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ከስልጣን በማንሳት አዲስ ፕሬዚዳንት ሾመ

  • sheger1021fm
  • Aug 15, 2024
  • 1 min read

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ከስልጣን በማንሳት አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ፕሬዚዳንት ሾመ፡፡


በምትካቸውም ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ተሹመዋል፡፡


የአመራር ለውጥ ያስፈለገበት ምክንያት በክልሉ በሠላምና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ዘርፍ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም የተቀመጡ አቅጣጫዎች ውስንነቶች በመታየታቸው ነው ተብሏል፡፡


በተጨማሪም ከስድስት ዓመት በላይ ክልሉን ሲመሩ የቆዩት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ለሌላ የፓርቲ ተልዕኮ በመፈለጋቸው መሆኑ ተነግሯል።

በምክር ቤቱ የተሾሙት ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ቀደም ሲል በጋምቤላ ክልል የሴቶችና ህፃናት ቢሮ በኃላፊነት እንዲሁም በሌሎች ቢሮዎች በኃላፊነት አገልግለዋል።


ወደዛሬው ሹመት እስከመጡበት ድረስም በኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር ሲል ክልሉ ተናግሯል።


የክልሉ ምክር ቤት በዛሬው አስቸኳይ ጉባኤው አዲስ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርም ሹመት አጽድቋል፡፡


በዚህም ጋትሏክ ሮን(ዶ/ር) የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መርጧል።

ጋትሏክ ሮን(ዶ/ር) በኢፌዴሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ ሆነው እያገለገሉ እንደነበር ክልሉ በማህበራዊ የተስስር ገጹ ላይ አስፍሯል።


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page