ነሐሴ 9፣2016 - ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ተሾሙ፡፡
- sheger1021fm
- Aug 15, 2024
- 1 min read
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ምክር ቤቱ ሹመቱን ያፀደቀው ዛሬ ባካሄደው 6ኛ የምርጫ ጊዜ 3ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው።
የአመራር ለውጥ ያስፈለገበት ምክንያት በክልሉ በሠላምና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ዘርፍ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም የተቀመጡ አቅጣጫዎች ውስንነቶች በመታየታቸው ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ከስድስት ዓመት በላይ ክልሉን ሲመሩ የቆዩት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ለሌላ የፓርቲ ተልዕኮ በመፈለጋቸው መሆኑ ተነግሯል።
በምክር ቤቱ የተሾሙት ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ቀደም ሲል በጋምቤላ ክልል የሴቶችና ህፃናት ቢሮ በኃላፊነት እንዲሁም በሌሎች ቢሮዎች በኃላፊነት አገልግለዋል።
ወደዛሬው ሹመት እስከመጡበት ድረስም በኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር ሲል ክልሉ ተናግሯል።
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comentários