ከእዚህ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የ''ቤቲንግ'' ወይም የስፖርት ውርርድ ቤት አይኖርም ሲል የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ተናገረ፡፡
የቢሮው ምክትል ሃላፊ ሚደቅሳ ከበደ፤ በተጠናቀቀው 2016 የበጀት ዓመት በከተማዋ የሚገኙ 4,118 የቤቲንግ(የስፖርት ውርርድ) ቤቶችን ዘግተናል፤ ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የውርርድ ወይም ቁማር ቤት አይኖርም ብለዋል፡፡
የቤቲንግ #ቁማር ስራን በዚህ ከተማ ላይ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም ሲሉ የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሚደቅሳ ከበደ አስረድተዋል፡፡
ልጆቻችን አዕምሯቸው በቁማር ምክንያት እየተበላሸ ነው፤ እቃም ጭምር ከቤት እየተሰረቀ እየተሸጠ ነው ሲሊ ሃላፊው ተናግረዋል።
ለትዳር ፊቺ ጭምር መነሻ ሆኗል እየተባለ #ቅሬታ ሲነሳ ነበር፤ ምላሽ ተሰጥቶታል ሲሉ ምክትል የቢሮ ሃላፈው ተናግረዋል፡፡
ማሸጉ ግብ አይደለም፤ በዘርፉ ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ ሌላ ስራ ቀይረው እንዲሰሩ ትዕዛዝ ተላልፏል ብለዋል።
አቶ ሚደቅሳ ቤት አከራይተው የነበሩ አከራዬችም ለሌላ ንግድ ወይም አገልግሎት በማከራየት አንዲጠቀሙ ተደርጓል ብለዋል፡፡
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከዚህ ቀደም የስፖርት የውርርድ ቤቶች በመዘጋታቸው ከፍተኛ ገቢ መንግስትን እንዳሳጣው መናገሩን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments