ነሐሴ 7፣2016 - ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት፤ ሁለተኛ ዙር ንግግር መጀመራቸው ተሰማ፡፡
- sheger1021fm
- Aug 13, 2024
- 1 min read
በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ለማርገብ በቱርክ አመቻችነት ሁለተኛ ዙር ንግግር መጀመሩን የተናገሩት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ነብዩ ተድላ ናቸው፡፡
ቃል አቃባዩ ለሩሲያው አርቲ(RT) በሰጡት ቃለ ምልልስ ንግግሩ መጀመሩን አንጂ የተወከሉትን ዲፕሎማቶች አልጠቀሱም፡፡
በሰኔ ወር መገባደጃ ላይ በተደረገው የመጀመሪያው ዙር ንግግር ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ እና የሶማሊያ አቻቸው አህመድ ፊቅ በተገኙበት መካሄዱ ይታወሳል፡፡
ከሶማሊያ የግዛቴ አካል ነች ከምትላት ሶማሌላንድ ጋር ኢትዮጵያ በወደብ ጉዳይ የመግባቢያ ስምምነት ከፈረመች ወዲህ ሁለቱ ሃገራት የገቡበትን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በንግግር ለመፍታት በሰኔ ወር ላይ ያደረጉት ንግግርም ተስፋ ሰጭ መባሉ ይታወሳል፡፡
ሀገራቱ ንግግራቸውን ለመቀጠል በተስማሙት መሰረት ሁለተኛውን ዙር ንግግር እያካሄዱ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments