ነሐሴ 6፣2016 የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መግቢያ ፈተና እስከ ነሐሴ10 ድረስ መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- Aug 12, 2024
- 1 min read
ትምህርት ሚኒስቴር የድህረ ምረቃ ትምህርት ለመማር ወጥ የመግቢያ ፈተና እንደ ሀገር አቀፍ መስጠት መጀመሩ ይታወሳል፡፡
የ2017 ዓ.ም የመግቢያ ፈተናውን ለመስጠት ተማሪዎችን ለመመዝገብ ከሀምሌ 24 እስከ ነሀሴ 5 ድረስ አቅዶ የነበረ ቢሆን ዛሬ ማለዳ ባወጣው መረጃ ምዝገባው ለ5 ተጨማሪ ቀናት ተራዝሟል፡፡
ፈተናውን መውደስ የሚፈልጉ የድህረ ምረቃ ተፈታኞች እስከ ተጠቀሰው ቀን በትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በተቀመጠው ሊክ አማካኝነት መመዝገብ ይችላሉ ሲል አሳስቧል፡፡
በግልም ሆነ በመንግስት የሁለተኛ ዲግሪ አልያም ሶስተኛ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ አመልካቾች ቅድሚያ ይህንን ፈተና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል ሲል የትምህርተ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Commentaires