top of page

ነሐሴ 6፣2016 - በገጠር፣ ልክ በከተማ በአዲስ አበባ እንዳለው ኑሮና ብልሃቱን የሚያቀላጥፉ የግኑኝነት መስመሮች እንደልብ አይገኝም

ዛሬም ድረስ ከከተማ የሚርቁ፣ ከተማ ብለን ከምንጠራቸው በየክልሉ ካሉት ከተሞች 45 ትም፣ 25ትም ኪሎ ሜትር ወደ ገጠር የሚዘልቁ ኑሮና ልማድ ያለባቸው አካባቢዎች አሉ።


በሀገር፤ መንገድ የሌለበት፣ የምሽት ብርሃን ኩራዝ የሆነበት፣ እረኛ ምን አለ ተብሎ መረጃ በሚቀባበልበት የገጠር መንደር የቴሌኮም መሰረተ ልማት እንደ ልብ አልተዘረጋም።


በገጠር፤ ልክ በከተማ፣ በአዲስ አበባ እንዳለው ኑሮና ብልሃቱን የሚያቀላጥፉ የግኑኝነት መስመሮች እንደልብ አይገኝም።


ኢትዮ ቴሌኮም በገጠር አካባቢ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላላገኙ 100 የገጠር ቀበሌና ወረዳዎች በመጀመርያው ምዕራፍ ባቀደው ጊዜና ወቅት አገልግሎቱን አጠናቆ አገልግሎት አስጀምሯል።


በዚህ ምዕራፍ የቴሌኮም አገልግሎት ተደራሽ ባልነበረባቸው ገጠራማ አካባቢዎች በመውረድ 100 የገጠር ሞባይል ኔትወርክ ጣቢያዎችን መገንባቱን ሰምተናል።


በዚህም በ305 የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች የሚኖሩ ከ903,000 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘት ችለዋል፡፡

ይህ የመጀመሪያ ምዕራፍ ፕሮጀክት በስኬት መጠናቀቅ ተከትሎ የቴሌኮም አገልግሎት ለማግኘት በአማካይ እስከ 20 ኪ.ሜ ያደርጉት የነበረውን ጉዞ ያስቀራል ተብሏል።


ይህ ፕሮጀክት ሲከናወን ኩባንያው ራቅ ባሉ የገጠር አካባቢዎች ላይ በመሄድ የመሬት አቀማመጥ፣ የመንገዶች ያለመኖር፣ የተበታተኑ ስፍራዎች እና የኃይል አቅርቦት እጥረት እንደፈተኑት ሰምተናል፡፡



ተህቦ ንጉሴ

Comments


bottom of page