top of page

ነሐሴ 6፣2016 - ‘’ምንዛሪ ገበያ መር አንዲሆን ለመወሰን ከዚህ የተሻለ ጊዜ የለም’’ በዓለም አቀፍ የእድገት ማዕከል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢኮኖሚስት ቴዎድሮስ መኮንን (ዶ/ር)

‘’የውጭ ምንዛሪ ገበያ መር አንዲሆን ለመወሰን ለኔ ከዚህ የተሻለ ጊዜ የለም’’ ሲሉ በዓለም አቀፍ የእድገት ማዕከል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢኮኖሚስት የሆኑት ቴዎድሮስ መኮንን (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡


የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ምንዛሪ ግብይት በገበያ እንዲመራ ከወሰነበት እለት ጀምሮ ውሳኔው ልክ ነው ልክ አይደለም በሚል ባለሞያዎችን ለሁለት ከፍሎ እያሟገተ ነው፡፡


ከፊሎቹ ውሳኔው ወቅቱን ያልጠበቀ በገበያ ላይም ከፍተኛ ቀውስ የሚፈጥር ነው ሲሉ ገሚሶቹ ደግሞ ኢትዮጵያ ዘግይታም ቢሆን የማይቀርላትን ማሻሽያ አሁን ማድረጉ ተገቢ ነው የሚል ክርክር ያቀርባሉ፡፡


ባለፈው ቅዳሜ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ(ኢዜማ) ይህን የተመለከተ ወይይት አካሂዷል፡፡


በወይይት ላይ የተጋበዙት በአለም አቀፍ የእድገት መዕከል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢኮኖሚስት የሆኑት ቴዎድሮስ መኮንን(ዶ/ር) ማሻሽያውን ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ጊዜ ለኔ የለም ይላሉ; ምክንያታቸውንም አስረድተዋል፡፡



ያሬድ እንዳሻው

Comments


bottom of page