top of page

ነሐሴ 6፣2016 - ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ፤ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ አተረፍኩ አለ።

  • sheger1021fm
  • Aug 12, 2024
  • 1 min read

ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከግብር በፊት ያስመዘገበው 1.25 ቢሊዮን ብር ትርፍ ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ27 በመቶ ብልጫ እንዳለው በሰጠው መግለጫ አስረድቷል።


ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም መመዘኛዎች  ራሱን እያሳደገ መምጣቱን የተናገረው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ፤ በአለም አቀፍና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተፈጠሩ እና ኢኮኖሚውን ሊረብሹ የሚችሉ ችግሮች በመቋቋም በትርፍ ጎዳና ላይ መቀጠሉን ጠቅሷል።

ባንኩ በአሁኑ ሰአት ከ 20,000 በላይ ባለአክሲዮኖች አሉኝ ያለ ሲሆን፤ በመላው ኢትዮጵያ የቅርንጫፎቹም ብዛት ከ225 በላይ መድረሳቸውን አስረድቷል።


ከመደበኛ የባንክ እንልግሎት በተጨማሪ የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆችን በመከተል ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ አራት ቅርንጫሮችን ጨምሮ በሁሉም ቅርንጫፎች በአንድ መስኮት ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት እየሰጠሁ እገኛለሁ ብሏል።


በዲጂታል መላ በመታገዝ ግሎባል ባንክ እትዮጵያ 24 ሰዓት ደንበኞቹን እያገለገለ እንደሆነም ተናግሯል።


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page