ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ለስራ እድል ፍለጋ ዜጎቻቸው ከሚሰደዱባቸው ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
የአለም አቀፉን የሰራተኞች ድርጅት(ILO) መረጃ በግብአትነት ተወስዶ በተሰራው በዚሁ ጥናትም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን አሁን #የእስራኤል_ጦርነት ያንዣበባቸው ሃገራትን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ይገኛሉ፡፡
የእስራኤሉ ጦርነት አድማሱን ያሰፋባቸዋል የሚል ስጋት ካጠላባቸው መካከል በሆነችው #ሊባኖስም በቁጥር ትንሽ የማይባሉ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ይነገራል፡፡
የተለያዩ የአለም ሀገራትም በተጠቀሰችው ሃገር ያሉ ዜጎቻቸውን ደህንነት ለማስጠበቅ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው፡፡
ኢትዮጵያስ ምን እያደረገች ነው? #የውጭ_ጉዳይ_ሚኒስቴርን በጉዳዩ ላይ አነጋግረናል፡፡
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments