top of page

ነሐሴ 30፣2016 - ''ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው ዝርፊያ እና ጥቃት ቀንሷል'' የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር

  • sheger1021fm
  • Sep 5, 2024
  • 1 min read

ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው ዝርፊያ እና ጥቃት ቀንሷል ሲል የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

ከዚህ ቀደም ጉዳት ለደረሰባቸው አሽከርካሪዎች ካሣ ለመስጠት መታሰቡን ሰምተናል፡፡


ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች በየመንገዱ በሚደርስባቸው ጥቃት ህይወታቸው እንደሚያልፍ፣ ዘረፋ እና እገታ እንደሚደርስባቸው ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።


በትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር የትራንስፖርት አገልግሎት እና ቁጥጥር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን፤ በድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰውን የእገታ እና የስርቆት እንዲሁም የሞት እና የአካል ጉዳትን ለመከላከል ድንበር ላይ ያሉ የፀጥታ አካላትን በቴክኖሎጂ በታገዘ አሰራር ቁጥጥር እንዲያደርጉ በማድረግ ዝርፊያዎች እና እገታዎች እንዲቀንሱ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል።


በአሽከርካሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት እና መሰል ጉዳቶች ቢቀንሱም አሁንም ችግሩ ሙሉ በሙሉ አልተቀረፈም የሚሉት አቶ በርኦ ይህን ችግር ለማቃለልም ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።


አያይዘውም ከዚህ ቀደም ጉዳት ለደረሰባቸው አሽከርካሪዎች ድጋፍ ለማድረግ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራም እየተከወነ መሆኑን ነግረውናል።


በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ባለው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በድንበር ተሻጋሪ የከባድ መኪና ሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸመው እገታ፣ ዘረፋ እና ግድያ ተባብሶ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 መናገሩ መዘገባችን ይታወሳል።


ፍቅሩ አምባቸው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page