top of page

ነሐሴ 30፣2015 -የካፒታል ገበያ ሲጀመር ድርጅቶች የብድር ሰነድ ሸጠው እንዲመነደጉ የሚያግዝ ስምምነት ተደርጓል


በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ሲጀመር ከመንግስት ባለፈ ድርጅቶች የብድር ሰነድ ሸጠው በፋይናንስ እንዲመነደጉ የሚያግዝ ስምምነት ተደርጓል።


በካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሥር የኢትዮጵያ መዋለነዋዮች ወደ ገበያ ሲገባ ከመንግስት ባለፈ ድርጅቶች የብድር ሰነድ ሽጠው በፋይናንስ እንዲመነደጉ የሚያግዝ ስምምነት ተደርጓል።


ይህንኑ ዓላማ እንዲያበረታ ዛሬ የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ከ international Finance Corporation/IFC ጋር በመተባበር ለመስራት ተፈራርመዋል።


በዚሁ ጉባኤ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ስምምነቱ መደረጉ ድርጅቶች እንዴት የእራሳቸውን ሰነድ ሽጠው ተጨማሪ ፋይናንስ ያግኙ በሚለው ዙሪያ ጥናትና መንገዶችን ለመለየት ያግዛል ብለዋል።


IFC በኢንቨስትመንትና በግብር ወይም በቴክኒክ ከማገዝ ባለፈ ይህ ገበያ እንዴት ይደግ በሚለው በኩል ጠቅለል ያለ ድጋፍ እንደሚያደርግ ሰምተናል።


ለምሳሌ የብድር ሰነድ ከተዘጋጀ በኋላ ገበያው አዋጭ ነው ወይስ? ምንድነው? የሚለውን ለመለየት IFC ከፊት ሆኖ የሙከራ ኢንቨስትመንት አድርጎ ገበያውን እንደሚያግዝ ዶ/ር ብሩክ ተናግረዋል።


በዛሬው ስምምነት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የቦርድ ሰብሳቢና የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ተገኝተዋል።


ካፒታል ገበያው በተለያዩ ምክንያቶች በፋይናንስ ያልተካተቱትን በተለይ ግብርናውና በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ለውጥ እንደሚያመጣ ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ ዋና ገዢው ተናግረዋል።


የካፒታል ገበያ ወደ ሥራ መግባት ተገቢ የአክሲዮን ቁጥጥር ስለሚደረግበት ለመንግስት፣ ለገበሬውና አነስተኛ እና ጥቃቅን የንግድ ቤቶች የሀገር ውስጥ ፋይናንስ እንዲያገኙ ያግዛል ተብሏል።


በዚህ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን እና አይ ኤፍ ሲ በጋራ የቦንድ ሽያጭን በማበርታት አብረው ይሰራሉ ተብሏል።


በመንግስት እና በግል የካፒታል ማሰባሰብ ላይ ላሉ ድርጅቶችም የቁጥጥርና የህግ መስመሮችን በመለየት ገበያው በኢትዮጵያ እንዲሰለጥን እንደሚተባበሩ ሰምተናል፡፡


በዛሬው ስምምነት የ IFC የፋይናንስ ተቋማት ቡድን የአፍሪካ ዳይሬክተርና ሌሎች የሀገር ቤት የፖሊሲ አማካሪዎች ተሳትፈዋል።



ተህቦ ንጉሴ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

댓글


bottom of page