top of page

ነሐሴ 3፣2016 - ዳሸን ባንክ ለውጭ ሀገር ጉዞና ለሀገር ቤት ግብይት የሚያግዙ ሁለት አዳዲስ ካርዶችን ወደ ቢዝነስ ማስገባቱን ተናገረ

ዳሸን ባንክ ለውጭ ሀገር ጉዞና ለሀገር ቤት ግብይት የሚያግዙ ሁለት የፋይናንሰ አገልግሎት የሚሰጡ አዳዲስ ካርዶችን ወደ ቢዝነስ ማስገባቱን ተናገረ።


ባንኩ ከዚህ ቀደም ያልሰራባቸው ሁለት አዳዲስ የፉይናንስ አገልግሎት ሰጪ ካርዶች “ሾፐርስ ክለብ ጋር ካርድ” እና “ትራቭለርስ ክለብ ካርድ” ይሰኛሉ።


ትራቭለርስ ክለብ ካርድ ግልጋሎቱ የጉዞ ዕቅዳቸውን ለማሳካትና ተያያዥ ጋር ጥቅሞችን ለማግኘት እንዲችሉ የሚያግዝ አገልግሎት ነው፡፡


ሾፐርስ ክለብ ካርድ ደግሞ በተደጋጋሚ ከፍተኛ ግብይት የሚፈጽሙ ደንበኞች በግብይት ወቅት ቅናሽ እንዲያገኙና የተሻለ አገልግሎት እንዲቀርብላቸው የሚያስችል ካርድ ነው ተብሏል።


አገልግሎቱ በዋናነት ደንበኞች የጉዞ ቴኬት ወጪን ለመሸፈን የሚያስችል የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ እና የተለያዩ የአገር ውስጥ ግብይቶችን ሲፈፅሙ ቅናሽ እንዲያገኙ የሚያስችል ካርድ መሆኑ ተሰምቷል።

ሁለቱም አገልግሎት የሚሰጡት ካርዶች ያለ ሂሳብ ደብተር የሚቀርቡ ናቸው።


ነገር ግን የክለቡ አባል በመሆን ሂሳብ በተናጠል ወይም በጋራ በመክፈት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ባንኩ አስረድቷል።


ለዚህ አገልግሎት የዳሽን ባንክ ደንበኞች ከ500,000 እስከ 2.5 ሚሊየን ብር የመጀመሪያ ተቀማጭ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።


ደንበኞች ይህን አገልግሎት ለማግኘት ቅድሚያ የተጓዦች ክለብ አባል መሆን የሚያስችል ሂሳብ መክፈት ይኖርባቸዋል።


በዚህ አገልግሎት የመሰረታዊ፣ ሰማያዊ፣ ብር፣ ወርቅ እና ፕላቲኒየም ደረጃ አባል መሆን ይችላሉ ተብሏል።


ደንበኞች የሸማቾች ክለብ አባል ለመሆን ከ50 ሺ 400 ሺ ብርየመጀመሪያ ተቀማጭ ገቢ በማድረግ በመሰረታዊ፣ሰማያዊ፣ ብር፣ወርቅ እና ፕላቲኒየም ደረጃዎች አባል መሆን እንደሚችሉም ሰምተናል።


የደንበኞችን አባልነት ለመጠበቅ የመጀመሪያ ተቀማጭ በዝግ ሂሳብ እንዲቀመጥ የሚደረግ ሲሆን ባንኩ በየወሩ በሚደረግ የቁጠባ መጠን ላይ እስከ 10 በመቶ የሚደርስ ወለድ ይከፍላል ተብሏል።


ደንበኞች በአገር ውስጥ ከባንኩ አጋር ከሆኑ ሆቴሎች፣ ሪዞርቶች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ የመዝናኛ ማዕከላት እናየጉዞ ወኪሎች ለሚያገኙት አገልግሎት የ5 በመቶ ቅናሽይደረግላቸዋል፡፡


የነዚህ ካርዶች ተጠቃሚዎች “የአሁን ይብረሩ” ቆይተው ይክፈሉ፣ የዱቤ አለ እና ሌሎች ባንኩ የሚሰጣቸው የብድር አገልግሎቶችተጠቃሚ እንዲሆኑ ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑን ባንኩ አስረድቷል፡፡


ደንበኞች ይህን ካርድ ለመጠቀም የታደሰ መታወቂያ ካርድ የቅርብ ጊዜ ፎቶ ግራፍ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርም ልትጠቁ ትችላላችሁ ተብላቹሀል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comentarios


bottom of page