top of page

ነሐሴ 3፣2016 - የአለም የክህሎት ተቋም፤ ኢትዮጵያን 88ኛ አባል አድርጎ ተቀበላት

  • sheger1021fm
  • Aug 9, 2024
  • 1 min read

የአለም የክህሎት ተቋም፤ ኢትዮጵያን 88ኛ አባል አድርጎ ተቀበላት፡፡


የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአለም ክህሎት ተቋም ኢትዮጵያን 88ኛ አባሉ አድርጎ እንደተቀበላት ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግሯል፡፡


መግለጫውን የሰጡት የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ኢትዮጵያ አባል ለመሆን 2 ዓመት ፈጅቶባታል ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ የአለም የክህሎት ተቋም አባል መሆኗ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፋይዳ እንዳለው ሚኒስትሯ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ትስስር ለመፍጠር የሞያ ልውውጥ በማድረግ ኢትዮጵያ አባል መሆኗ ይረዳታል ተብሏል፡፡


ኢትዮጵያ በመድረኩ ሙያ ተቀባይ ብቻ ሳትሆን ክህሎት የምታካፍለበትም መድረክ ይሆናል ብለን እንጠብቃለን ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡


በመጪው መስከረም ፈረንሳይ ላይ የሚዘጋጀው 47ተኛው አለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ ኢትዮጵያ በሶስት መስኮች ትሳተፋለች ተብሏል፡፡


ፈርኒቸር ፣ ማሽን እና አይሲቲ 3ቱ ኢትዮጵያ የምትወዳደርባቸው ሞያዎች ናቸው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በየ2 ዓመቱ የሚካሄደውንና አባል የሆነችበትን የክህሎት ውድድር ለማዘጋጀት እቅድ እንዳላት ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡


የአለማቀፉን የክህሎት ተቋም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ 10 ሀገራትን በአባልነት ተቀብሏል፡፡


ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ፣ ደቡብ አፊሪካ፣ ጋና፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ እና ሞሮኮ የድርጅቱ አባል ሀገራት ናቸው፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page