የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን ለመክፈት የስራ ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል እንደጀመረ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተናገረ።
ማዕከላዊ ባንኩ ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ ከሐምሌ 22 ጀምሮ ስራ ላይ በዋለው የውጭ ምንዛሬ መሰረት የውጭ ምንዛሬ መስራት የምትፈልጉ ማመልከቻ ማስገባት ትችላላችሁ ብሏል።
የውጭ ምንዛሬ ቢሮ ለመክፈት መስፈርቱን አሟልተው የሚገኙ፤ የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው፣ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የሚኖሩ እንዲሁም የሌላ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።
የግል የውጭ ምንዛሮ ቢሮዎች እንዲከፈቱ የስራ ፈቃድ መሰጠቱ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ለመክፈት እና ዘርፉን በቀጣይ አመታት ተወዳዳሪ ለማድረግ ጠቃሚ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ሞማ ምህረቱ ተናገረዋል።
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comentários