''አካል ጉዳተኞች በፖለቲካው እንዲሳተፉ መጠየቅን ጨምሮ ዋና ዋና ያልኳቸውን ሶስት አጀንዳዎች ለምክክር ኮሚሽን አስረክቢያለሁ'' ሲል የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ተናገረ፡፡
ፌዴሬሽኑ ውስብስብ ያልተፈቱ ችግሮች ያሉብን እኛ ስለሆንን አስቀድመን የለየናቸውን አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ እንዲመከርባቸው እና መፍትሄ እንዲገኙ አስረክቢያለሁ ሲል ተናግሯል፡፡
ከህግ መንግስት ጀምሮ ፖሊሲዎች ፤ህጎች ፤አዋጆች አካል ጉዳተኛን ታሳቢ ያደረጉ እሱን ያካተቱ እንዲሆኑ የሚጠይቀው አንደኛው አጀንዳ እንደሆነ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዳይሬክተር አባይነህ ጉጆ ንግረውናል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ አካል ጉዳተኞች በፖለቲካው እንዲሳተፉ ውሳኔ ሰጪ ቦታዎች ላይ እንዲቀመጡ የሚጠይቅ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
በዚህም ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጋ ቁጥር ያለው አካል ጉዳተኛው በፖለቲካው ሊሳተፍ ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡
የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ የሚመራ ራሱን የቻለ ተቋም እንዲኖር የሚጠይቀው ደግሞ ሶስተኛ አጀንዳ ሆኖ ለምክክር ኮሚሽን ቀርቧል ሲል ፌደሬሽኑ ተናግሯል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comentarios