top of page

ነሐሴ 29፣2016 - መጠለያው ትምህርት ቤት መሆኑን የተናገሩት ተፈናቃዮቹ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ሊጀመር ቀናቶች የቀሩት በመሆኑ ስጋት ውስጥ ገብተናል ይላሉ

በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ የመሬት መንሸራተት አደጋ በማጋጠሙ ምክንያት ቀያቸውን ለቀው በመጠለያ ውስጥ ላሉ ከ300 በላይ ነዋሪዎች የሚደረገው የምግብ አቅርቦት ቀንሷል ተባለ፡፡


ከዚህ ቀደም ተፈናቃዮቹ ሲረዱ የነበረው ከከተማዋ ነዋሪዎች በሚገኝ እና በከተማዋ ከሚገኙ ተቋማት እንደነበር ተነግሯል፡፡


ይህንን የተናገረው የደሴ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ ነው፡፡


ከአደጋው ሸሽተው በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ያሉት ነዋሪዎችም የሚሉትም ይህንኑ ነው፡፡

መጠለያ ጣቢያው ትምህርት ቤት መሆኑን የተናገሩት ተፈናቃዮቹ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ሊጀመር ቀናቶች የቀሩት በመሆኑ ስጋት ውስጥ ገብተናል ይላሉ፡፡


በሌላ በኩል ከድጋፍ ሰጭዎች የሚገኘው የምግብ እርዳታ ከጊዜ ወደ ጊዜ መቀነስ፣ የተጠለሉበት ቦታ ምቹ አለመሆን እና ሌሎችም ችግሮች እንዳሉባቸው የተፈናቃዮቹ ተወካዮች ይናገራሉ፡፡


የመሬት መንሸራተት አደጋውን ሸሽተው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ካሉ ነዋሪዎችም ህፃናት እና ሴቶች እንደሚበዙ የደሴ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ይናገራል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ...



ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


bottom of page