top of page

ነሐሴ 28፣2016 - ዩኒቨርሲቲዎች ከ4 ዓመት በፊት በተልዕኮና ትኩረት ተለይተው ይደራጃሉ ቢባልም ዛሬም ድረስ እውን አልሆነም

ለዚህ ደግሞ የትምህርት ሚኒስቴር ክትትል ማነስ እና የዩንቨርስቲ አመራሮች ለስራው የሰጡት ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ነው፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርስቲዎችን በትምህርት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በምርምር፣ በአጠቃላይ ትምህርት እና የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በሚል በአምስት ዘርፍ ተከፍለዋል፡፡


ይህ ተልዕኮ በ2016 ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡


የትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና(ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ በዚህ መንገድ ሳይዳጁ የቆዩበት ምክንያት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች ለስራው የሰጡት ትኩረት አነስተኛ መሆን፣ የትምህርት ሚኒስቴር ክትትል ደካማ መሆን ነው ብለዋል፡፡


ዶክተር ኤባ ከ51 ዩኒቨርሺቲዎች መካከል 4 ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮና ትኩረት ተደራጅተው በ2017 በጀት ዓመት ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ ይላሉ፡፡


እነዚህ ዩኒቨርስቲዎች የሰው ኃይል አደረጃጀታቸውና የትምህርት ፕሮግራሞቻቸው በተመደቡበትም መስክ አሰናድተው መጨረሳቸው ሰምተናል፡፡


ታዲያ ቀሪ 47 የሚሆኑትስ እስከ መች ድረስ ወደዚህ ሥርዓት ይገባሉ ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ ዶክተር ኤባ ሲመልሱ በ2017 ቀሪዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ከ5ቱ ወደ በአንዱ ዘርፍ ይጠቀለላሉ፡፡

ለዚህም የሚሆን ስራ በየጊዜው የሚፈፁሙት እቅድ ትምህርት ሚኒስቴር ሰጥቷቸዋል እሱን እንከታተላለን ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡


በዚህ እቅድ መሰረት የሚፈፅሙት ትምህርት ሚኒስቴር የማበረታቻ ሽልማት አዘጋጅቷል ተብሏል፡፡


በ2017 መጨረሻ ስራውን ፈፅሞ ያልተገኘ ዩኒቨርስቲዎች በሚገባ ይመረመራልም ብለዋል፡፡


ከዚህ ቀደም አንድ ዩንቨርስቲ ውስጥ ከ200 እስከ 300 ፕሮግራሞችን ይዞ ያስተምር ነበር የሚሉት ዶክተር ኤባ ይህም ትኩረታቸው እንዲበተንና ተፎካካሪ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡


ተቋማቱ በተልዕኮና በትኩረት ሲመደቡ ከሚያስተምሩት ውጪ ያሉ ፕሮግራሞች ይታጠፋሉ፡፡


አሰራሩ ተግባራዊ ሲሆን ዩኒቨርስቲዎች ተጨማሪ በጀት እንዲያመነጩና ውጤታማ ጥናትና ምርምር እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል የዶክተር ኤባ እምነት ነው፡፡


በረከት አካሉ

Comments


bottom of page