top of page

ነሐሴ 28፣2016 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደርገውን በረራ እንዳቋረጠ ተናገረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደርገውን በረራ እንደሚያቋርጥ ተናገረ።


አየር መንገዱ ከነሐሴ 28፣2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ እንደሚያቋርጥ የተናገረው አመሻሹን ባወጣው መጎለጫ ነው።


በረራው የሚቋረጠውም ከአቅሙ በላይ በሆነ አስቸጋሪ የስራ ሁኔታ ምክንያት መሆኑንም አስረድቷል።


በዚህም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር ትኬት የቆረጡ መንገደኞች  ያለምንም ተጨማሪ ወጪ በሌሎች አየር መንገዶች ጉዟቸውን እንዲያደርጉ ጥረት እንደሚያደርግሞ ጠቅሷል።

የትኬት ገንዘባችን ይመለስ የሚሉ ካሉም ለቲኬታቸው ሙሉ ገንዘብ ተመላሽ እንደሚያደረግ አስታውሷል።


በበረራው መቋረጥ ምክንያት  ለሚፈጠረው መጉላላት  ይቅርታ እንይቃለሁ ያለው አየር መንገዱ  ስለሚረዱትም አመስግኗል።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም 20፣2017 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ኤርትራ መብረር አንደማይችል ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በደብዳቤ አንደተናገረው መናገሩ ይታወሳል።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ማብራሪያ እየፈለገ መሆኑን ተናግሮ  ማንኛውንም ችግር በሰላማዊ መንገድ እና በፍጥነት ለመፍታት ቁርጠኛ ነኝ ሲል ሐምሌ 17፣2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።


የኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኞች ከመስከረም 20፣2017 ጀምሮ ወደ ኤርትራ የሚደርጉትን በረራ አንደሚያግድ የተናገረው የተጓዦች ሻንጣ ይሰረቃል፣ተደጋጋሚ የበረራዎች እና የሻንጣዎች መዘግየት ያገጥማል በሚል ምክንያት አንደሆነ ተዘግቧል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

Comments


bottom of page