የተፈጥሮ አደጋዎች በሚደርሱበት ወቅት ዩኒቨርሲቲዎች ችግር ፈቺ ለመሆን ቀዳሚ መሆን አለባቸው ሲሉ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ግን ይህንን ሲያደርጉ አይታይም ብለዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ችግር ፈቺዎች አደሉም ይላሉ፡፡
ይህ እንዲሆን ካደረጉት መካከል ደግሞ ዩኒቨርስቲዎች በመንግስት በጀት ስለሚንቀሳቀሱ ነው መባሉንም ሰምተናል፡፡
የሚያስጠኑት ጥናት የተማሪዎች የመመረቂያ ጹሁፍ ከወረቀት አልፎ ስራ ላይ ሲውል አይታይም የሚሉት ባለሞያው ዩኒቨርስቲዎች በራሳቸው በጀት የሚንቀሳቀሱ ቢሆን ኖሮ ለገቢያቸው ሲሉ ተግባር ላይ የሚውል ጥናት እና ምርምር ያደርጉ ነበር ብለዋል፡፡
ጥናቶች ሲደረጉ ቀድሞ የሚሆነውን ማረጋገጥ እና አንድ ችግር ከደረሰም በኃላ መፍትሄ ይዞ መምጣት እንዳለባቸው ተነግሮዋል፡፡
ማርታ በቀለ
Comments