ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ወደ ብሔራዊ ባንክ፤ በየዓመቱ የሚገባው የወርቅ መጠን ከ800 ኪሎ ግራም ወደ 90 ኪሎ ግራም ወርዷል ተባለ፡፡
‘’ከ2000 እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ የተሻለ የወርቅ መጠን ወደ ብሔራዊ ባንክ ይገባ ነበር ከ2 ዓመታት ወዲህ ግን ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን በእጁ እየቀነሰ ነው’’ ሲሉ የክልሉ የማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ገ/ማርያም ሰጠኝ ነግረውናል፡፡
‘’በ2002 እና 2003 ዓ.ም እስከ 800 ኪሎ ግራም ወርቅ ከአካባቢው ወደ ብሔራዊ ባንክ ይገባ እንደነበር አቶ ገ/ማርያም ጠቅሰው ይህ መጠን እስከ 2015 ዓ.ም የቀጠለ ነበር’’ ብለዋል፡፡
ይሁንና ከ2015 ወዲህ ባሉት 2 ዓመታት ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን ከ90 ኪሎግራም ያልተሻገረ ነው ብለዋል፡፡
‘’ከአምራቾች እና ከአቅራቢዎች ጋር በነበረን ውይይት ለብሄራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን ነው እንጂ ምርቱ እንዳልቀነስ ተረድተናል’’ ሲሉ የክልሉ የማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ገ/ማርያም ሰጠኝ ነግረውናል፡፡
‘’እስካሁን መስኩ በዘመናዊ መሳሪያ ሳይታገዝ ከፍተኛ የወርቅ መጠን ወደ ብሔራዊ ባንክ ይገባ ነበር አሁን ግን መጠቆሚያ መሳሪያና በማጠቢያ ማሽን ታግዞ ለብሔራዊ ባንክ የሚቀርበው የወርቅ መጠን በእጅጉ ዝቅተኛ ነው’’ ተብሏል፡፡
ህገ - ወጥ የወርቅ ንግድ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለሚገባው የወርቅ መጠን መቀነስ ዋነኛው ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
በግራም እስከ ሺህ ብር እየጨማሩ ህገ-ወጦች ከወርቅ አቅራቢዎች እና አምራቾች በመግዛታቸው ወደ በብሄራዊ ባንክ የሚገባው ወርቅ እንዲቀንስ አድርጓል ተብሏል፡፡
በቂ ቁጥጥርና ምቹ ሁኔታ አለመኖሩ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለሚገባው የወርቅ መጠን መቀነስ ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገ/ማርያም ሰጠኝ ነግረውናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
コメント