በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከ 4,000 በላይ ትምህርት ቤቶች ጉዳት ሲደርስባቸው ከ 3 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ሳያገኙ ቆይተዋል፡፡
የሰሜኑ ጦርነት አለፍ ሲልም አሁን ላይ በክልሉ የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭት በርካታ የትምህርት ተቋማትን ክፉኛ እንደጎዳው ተነግሯል፡፡
ለዓመታት አለመረጋጋት ያልተለየው የአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀመጡ አድርጓቸዋል፡፡
በ2015 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን 1,019 የመጀመሪያ ደረጃ እና 59 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነበሩ፡፡
አሁን ግን በተለይም አብዛኞቹ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸው በክልሉ ያለውን የትምህርት ዘርፍ መጎዳት ያሳያል የሚለው የዞኑ ትምህርት መምሪያ ትምህርት ቤቶቹ በካምፕነት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ተናግሯል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ፅህፈት ቤት በበኩሉ በ2016 ዓ.ም በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከ3,000 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደነበር ተናግሯል፡፡
ከ2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ደግሞ ለ2016 የትምህርት ዘመን ያልተመዘገቡ ናቸው የተባለ ሲሆን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ደግሞ ከ 4,000 በላይ ትምህርት ቤቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ሲነገር ሰምተናል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Коментарі