top of page

ነሐሴ 28፣2016 - ለመሆኑ ገበያው ተጀምሯል ከተባለ የሚቀሩ ስራዎች ምንድናቸው?

ኢትዮጵያ ሁሉንም በፋይናንስ ያካትትልኛል ያለችውን መንገድ ይዛለች።


ከዚህ ባሻገር የሀብት ማሰባሰብያ የኢኮኖሚና ቢዝነስ ማፈናጠርያ ይሆናል የተባለው የካፒታል ገበያ ወደ ስራ ገብቷል።


ሀብት እንዲፈጠር፣ ኢንቨስትመንት እንዲበረታ ወደ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወደ ስራ የገባው የካፒታል ገበያ ስራና መከናወን በደንብ በገበያው እንዲላወስ በብርቱ እየሰራ መሆኑ ተሰምቷል።


ከተቋቋመ 3 ዓመት የሞላው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በእግሩ ቆሞ ለገበያው የሚያስፈልጉ ስራዎችና የቴክኖሎጂ ዝግጅቱም እየበረታ፣ ፍቃድም እየተሰጠ ነው።


ለመሆኑ ገበያው ተጀምሯል ከተባለ የሚቀሩ ስራዎች ምንድናቸው?


ሃና ተኸልቁ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ናቸው።


እሳቸው ለህግ የሚቀርቡ ሰነደ መዋለነዋዮችን የሚያወጡ ድርጅቶች ጋር ህጉ በሚያዘው መንገድ ሰነዶቻቸውን እንዲያዘጋጁ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።


ተህቦ ንጉሴ

Comentarios


bottom of page