top of page

ነሐሴ 27፣2016 - የዳስነች ወረዳ ነዋሪዎችን መንግስት በዘላቂነት እንዲያቋቁም ተጠየቀ

በተደጋጋሚ በውሃ መጥለቅለቅ ለአደጋ እየተጋለጡ ያሉት የዳስነች ወረዳ ነዋሪዎችን መንግስት በዘላቂነት እንዲያቋቁም ተጠየቀ፡፡


ጥያቄውን ያቀረበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ነው፡፡


ኮሚሽኑ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳስነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ ከመጠን በላይ በመሙላቱ እና መደበኛ የመፍሰሻ መስመሩን ለቆ በመውጣቱ ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ የአካባቢው ነዋሪዎችን እና ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብት አያያዝ በተመለከተ ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ክትትል ሳደርግ ቆይቻለሁ ብሏል፡፡

በዚህም በ12 መጠለያ ጣቢዎች ለሚገኙ ከ79,00 ሺህ በላይ ለሆኑ ተፈናቃዮች ወቅቱን የጠበቀ እና በቂ ድጋፍ እየደረሳቸው አለመሆኑን ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡


ቀደም ብለው ከተፈናቀሉትም በተጨማሪ ደግሞ ባለፈው በነሐሴ ወር ጀምሮ በአካባቢው በጣለው ዝናብ የኦሮሞ ወንዝ ሞልቶ መደበኛ መስመሩንም ለቆ ወጥቶ ከቱርካና ሐይቅ ጋር በመቀላቀሉ የዳስነች ወረዳ ዋና ከተማ በሆነው የኦሞራቴ ከተማ እንዲሁም በሌሎችም ቦታዎች በውሃ የመጥለቅለቅ ስጋት መኖሩን ኮሚሽኑ ጠቅሷል፡፡


በዚህም በተለይ በባዶ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያሉ 2,744 ተፈናቃዮች ለዳግም መፈናቀል ተዳርገዋል ተብሏል፡፡


በሌላ በኩል ሊቀርብላቸው የነበረው የንጹሃን ውሃ አቅርቦት ተቋርጦ ንጹህናው ያልተጠበቀውን የኦሞ ወንዝ ውሃ ለመጠጥነት እየተጠቀሙ ነው ተብሏል፡፡


በተጠለሉበት ቦታም በቂ የመፀዳጃ አገልግሎት መስጫ የለም የተባለ ሲሆን የኮሌራ በሽታን ጨምሮ የጤና ስጋት መኖሩን ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡


በመሆኑም የአካባቢው ሰዎችን ከተጨማሪ አደጋ ለመታደግ በዘላቂነት ማቋቋም ያሻል ሲል ኢሰመኮ ምክረ ሀሳብ ሰጥቷል፡፡


በተጨማሪም ለጊዜው ዳግም መፈናቀል እንዳይከሰት የተጀመሩ ስራዎችን እንዲበረክቱ እና የተለያዩ በሽታዎችን የመከላከል ስራም እንዲከወን ተጠይቋል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page