top of page

ነሐሴ 26፣2015 - አይቴል ሞባይል አዲስ ስሪቱን ቅንጡ የሞባይል ቀፎ በኢትዮጵያ ገበያ ማቅረቡን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Sep 1, 2023
  • 1 min read

አዲስ ስሪቱ የአይቴል ኩባንያው ሞባይል ቀፎ ኤስ 23+ ሞዴል መሆኑን ተናግሯል፡፡


የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከሚያቀርቡ ታላላቅ የሞባይል አምራች ኩባያዎች አንዱ የሆነው አይቴል ሞባይል ለገበያ ያበቃው ኤስ 23+ ሞዴል ለኩባንያው አዲስ ስሪት መሆኑን ተናግሯል፡፡


አዲሱ ሞዴል በቴክኖሎጂ እና ዲዛይን ልዩ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡


የዘመነ የካሜራ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ወይንም ሰው ሰራሽ ክህሎት የሚደገፈው ኢስ23+ ሞዱል የፊትለፊት 32 ሜጋ ፒክስል እና ዋናው ኃላ ካሜራ 50 ሜጋ ፒክስል ካሜራ እንዳለው ተጠቅሷል፡፡


ይህም ጥራት ያላቸውን ምስሎች በዝቅተኛ ብርሀን ውስጥም ሆነ በርቀት ቁልጭ አድርጎ ማንሳት የሚያስችል አቅም አለው ተብሎለታል።


አዲሱ አይቴል ኤስ 23+ 16ጂቢ ራም ከ 256 ጂቢ የሜሞሪ የተገጠመለት ሲሆን ፣ባለ 5000 ሚሊ አሚፒር ባትሪም አለው፡፡


ኤስ 23+ የሞባይል ሞዴል ለምጀመሪያ ጊዜ ለዓለም ገበያ ከመቅረቡ በፊት ኢትዮጵያን መርገጡ ታውቋል፡፡


አይቴል ሞባይል በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ በትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያ ስር የሚመረት ነው፡፡



ንጋቱ ሙሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page